2 ጢሞቴዎስ 1:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 እርሱ እኛ ስላደረግነው መልካም ሥራ ሳይሆን በራሱ ፈቃድና በጸጋው አዳነን፤ ለቅድስናም ጠራን፤ ይህንንም ጸጋ ከዘመናት በፊት በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ሰጠን። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 እኛ ስላደረግነው አንዳች ነገር ሳይሆን፣ ከዕቅዱና ከጸጋው የተነሣ ያዳነን፣ ወደ ቅዱስ ሕይወትም የጠራን እርሱ ነው። ይህም ጸጋ ከዘላለም ዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ ተሰጠን፤ See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 እንደ ሥራችን መጠን ሳይሆን እንደ ራሱ ዕቅድና እንደ ጸጋው መጠን አዳነን፥ በቅዱስም አጠራር ጠራን፤ ይህም ጸጋ ከዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ ተሰጠን፤ See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 ያዳነን በቅዱስም አጠራር የጠራን እግዚአብሔር ነውና፤ ይህም እንደ ራሱ አሳብና ጸጋ መጠን ነው እንጂ፥ እንደ ሥራችን መጠን አይደለም፤ ይህም ጸጋ ከዘላለም ዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ ተሰጠን፤ See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 ያዳነን በቅዱስም አጠራር የጠራን እግዚአብሔር ነውና፥ ይህም እንደ ራሱ አሳብና ጸጋ መጠን ነው እንጂ እንደ ሥራችን መጠን አይደለም፤ ይህም ጸጋ ከዘላለም ዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ ተሰጠን፥ See the chapter |