| 2 ሳሙኤል 8:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 በመላው ኤዶም ብዙ የጦር ሰፈሮችን አቋቋመ፤ በዚያም የሚኖሩ ሰዎች የእርሱ ተገዢዎች ሆኑ፤ እግዚአብሔር ዳዊትን በሄደበት ስፍራ ሁሉ ድልን ሰጠው።See the chapter አዲሱ መደበኛ ትርጒም14 በመላው ኤዶም የጦር ሰፈሮችን አቋቋመ፤ ኤዶማውያንም ሁሉ ለዳዊት ተገዙ፤ እግዚአብሔርም ዳዊትን በሄደበት ሁሉ ድልን ሰጠው።See the chapter መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 በመላው ኤዶም የጦር ሰፈሮችን አቋቋመ፤ ኤዶማውያን ሁሉ ለዳዊት ተገዙ፤ ጌታም ዳዊት በሄደበት ስፍራ ሁሉ ድልን ሰጠው።See the chapter የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 መላዋን ኤዶምያስን ይጠብቁ ዘንድ በኤዶምያስ ሁሉ ጭፍሮችን አኖረ፤ ኤዶማውያንም ሁሉ ለንጉሥ ዳዊት ገባሮች ሆኑ፤ እግዚአብሔርም ዳዊትን በሚሄድበት ቦታ ሁሉ ጠበቀው።See the chapter መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 በኤዶምያስ ሁሉ ጭፍሮች አኖረ፥ ኤዶማውያንም ሁሉ ለዳዊት ገባሮች ሆኑ፥ እግዚአብሔርም ዳዊት በሚሄድበት ሁሉ ድልን ሰጠው።See the chapter |