Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 23:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 በመከር ጊዜ መጀመሪያ ላይ ከሠላሳው ኀያላን በተለይ ሦስቱ ዳዊት ወዳለበት ወደ ዐዱላም ዋሻ ወረዱ፤ ከፍልስጥኤማውያን ሠራዊት ጥቂቱ ክፍል በራፋይም ሸለቆ ሰፍሮ ነበር፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 በመከር ወራት፣ የፍልስጥኤም ሰራዊት በራፋይም ሸለቆ ሰፍሮ ሳለ፣ ከሠላሳዎቹ አለቆች ሦስቱ ዳዊት ወዳለበት ወደ ዓዶላም ዋሻ መጡ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ከሠላሳውም አለቆች ሦስቱ ወርደው በመከር ጊዜ ወደ ዳዊት ወደ ዓዱላም ዋሻ መጡ፥ የፍልስጥኤማውያንም ጭፍራ በራፋይም ሸለቆ ሰፍሮ ነበር።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ከሠ​ላ​ሳ​ውም አለ​ቆች ሦስቱ ወር​ደው ወደ ቃሶን ወደ ዳዊት ወደ አዶ​ላም ዋሻ መጡ፤ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ጭፍራ በራ​ፋ​ይም ሸለቆ ሰፍሮ ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ከሠላሳውም አለቆች ሦስቱ ወርደው በመከር ጊዜ ወደ ዳዊት ወደ ዓዶላም ዋሻ መጡ፥ የፍልስጥኤማውያንም ጭፍራ በራፋይም ሸለቆ ሰፍሮ ነበር።

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 23:13
9 Cross References  

ፍልስጥኤማውያንም በራፋይም ሸለቆ ሰፍረው ለዝርፊያ ተበታትነው ተሰማሩ።


ዳዊት ከጋት ከተማ ሸሽቶ በዐዱላም ከተማ አጠገብ ወደሚገኝው ወደ አንድ ዋሻ ሄደ፤ ወንድሞቹና ሌሎቹም ቤተሰቦቹ ይህን በሰሙ ጊዜ ወደዚያ ሄደው ከእርሱ ጋር ተቀላቀሉ፤


የመሪሳ ሕዝብ ሆይ! ወራሪ ጠላት አመጣባችኋለሁ፤ የተከበሩ የእስራኤል መሪዎችም በዐዱላም ዋሻ ይሸሸጋሉ።


እስራኤል እህሉ ታጭዶ መከር ከተሰበሰበ በኋላ ባዶውን እንደሚቀር እርሻ ትሆናለች፤ ከመከር በኋላ የተራቈተ የራፋይምን ሸለቆም ትመስላለች።


ፍልስጥኤማውያን ወደ ራፋይም ሸለቆ መጥተው ወረሩአት፤


ከዚህ በኋላ ፍልስጥኤማውያን ወደ ራፋይም ተመልሰው እንደገና ሰፍረው ለዝርፊያ ተሰማሩ።


ያርሙት፥ ዐዱላም፥ ሶኮህ፥ ዐዜቃ፥


ሊብና፥ ዐዱላም፥


Follow us:

Advertisements


Advertisements