Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 2:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ከዚህ በኋላ ኢዮአብ እምቢልታውን ነፋ፤ ሰዎችም ሁሉ ቆሙ፤ ከዚያ በኋላ እስራኤልን አላሳደዱም፤ ጦርነቱንም አልቀጠሉም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ስለዚህ ኢዮአብ ቀንደ መለከቱን ነፋ፤ ከዚያም በኋላ ሰዎቹ በሙሉ እስራኤልን ማሳደዱን ተው፤ ውጊያውም በዚሁ አበቃ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ስለዚህ ኢዮአብ ቀንደ መለከቱን ነፋ፤ ከዚያም በኋላ ሰዎቹ በሙሉ እስራኤልን ማሳደዱን ተዉ ውጊያውንም አቆሙ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ኢዮ​አ​ብም ቀንደ መለ​ከት ነፋ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ተመ​ለሰ፤ ከዚ​ያም በኋላ እስ​ራ​ኤ​ልን አላ​ሳ​ደ​ዱ​አ​ቸ​ውም፤ ደግ​መ​ውም አል​ተ​ዋ​ጉም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ኢዮአብም ቀንደ መለከት ነፋ፥ ሕዝቡም ሁሉ ቆመ፥ ከዚያም በኋላ እስራኤልን አላሳደደም፥ ሰይፍም አላደረገም።

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 2:28
5 Cross References  

ኢዮአብም “አንተ ይህን ቃል ባትናገር ኖሮ የእኔ ሰዎች እስከ ነገ ጠዋት ወንድሞቻቸውን ከማሳደድ እንደማይገቱ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ” ሲል መለሰለት።


በዚህ ዐይነት በሳኦል ቤተሰብና በዳዊት ቤተሰብ መካከል የሚካሄደው ጦርነት ለረጅም ጊዜ ቈየ፤ ሆኖም ዳዊት እየበረታ ሲሄድ የሳኦል ቤተሰብ እየተዳከመ ሄደ።


ኢዮአብ ጦርነቱ ይቆም ዘንድ እምቢልታ እንዲነፉ አዘዘ፤ ወታደሮቹም እስራኤላውያንን ከማሳደድ ተመልሰው መጡ፤


ዮናታን ጌባዕ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በፍልስጥኤማውያን ላይ አደጋ ጣለ፤ ፍልስጥኤማውያንም ሁሉ ይህን ወሬ ሰሙ፤ ሳኦልም መልእክተኞችን ልኮ በሀገሩ ሁሉ እምቢልታ በማስነፋት ዕብራውያን ለጦርነት ጠራ።


ይህንንም ዕቅድ በተግባር ለመግለጥ ወደ ከተማይቱ ሕዝብ ሄደች፤ እነርሱም የቢክሪን ልጅ የሺባዕን ራስ ቈርጠው በግንቡ ላይ ለኢዮአብ ወረወሩለት፤ እርሱም ወታደሮቹ ከተማይቱን ለቀው ይወጡ ዘንድ ምልክት እንዲሆን እምቢልታ ነፋ፤ እነርሱም ወደየቤታቸው ተመለሱ፤ ኢዮዓብም ንጉሡን ለማግኘት ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements