2 ሳሙኤል 2:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም23 ዐሣሄል ግን አሁንም ማሳደዱን ሊተው አልፈቀደም፤ ስለዚህ አበኔር ጦሩን ወደ ኋላው ወርውሮ ሆዱ ላይ ሲሽጥበት ጫፉ ዘልቆ በጀርባው ወጣ፤ ዐሣሄልም መሬት ላይ ወድቆ ሞተ፤ ሬሳው በተጋደመበት ስፍራ የሚያልፍ ሰው ሁሉ በአጠገቡ ቆሞ ይመለከተው ነበር። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም23 አሣሄል ግን መከታተሉን አልተወም፤ ስለዚህ አበኔር በጦሩ ጫፍ ሆዱን ወጋው፣ ጦሩም በጀርባው ዘልቆ ወጣ፤ አሣሄልም እዚያው ወደቀ፤ ወዲያው ሞተ። እያንዳንዱም አሣሄል ወድቆ ወደ ሞተበት ስፍራ ሲደርስ ይቆም ነበር። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)23 አሣሄል ግን ማሳደዱን አልተወም፤ ስለዚህ አበኔር በጦሩ ጫፍ ሆዱን ወጋው፥ ጦሩም በጀርባው በኩል ወጣ፤ አሣሄልም እዚያው ወደቀ፤ ወድቆም በነበረበት ስፍራ ሞተ። እያንዳንዱም ሰው አሣሄል ወድቆ ወደ ሞተበት ስፍራ ሲደርስ ይቆም ነበር። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)23 ነገር ግን ከእርሱ ፈቀቅ ይል ዘንድ እንቢ አለ። አበኔርም በጦሩ ጫፍ ወገቡን ወጋው፤ ጦሩም በኋላው ወጣ፤ በዚያም ስፍራ ወድቆ በበታቹ ሞተ። አሣሄልም ወድቆ በሞተበት ስፍራ የሚያልፍ ሁሉ ይቆም ነበር። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)23 ነገር ግን ከእርሱ ፈቀቅ ይል ዘንድ እንቢ አለ፥ አበኔርም በጦሩ ጫፍ ሆዱን ወጋው፥ ጦሩም በኋላው ወጣ፥ በዚያም ስፍራ ወድቆ ሞተ። አሣሄልም ወድቆ በሞተበቱ ስፍራ የሚያልፍ ሁሉ ይቆም ነበር። See the chapter |