2 ሳሙኤል 10:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 ዳዊትም ይህን በሰማ ጊዜ የእስራኤላውያንን ወታደሮች ሁሉ በአንድነት አሰባስቦ የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻገረ፤ ከዚያም ሶርያውያን ወደ ሰፈሩበት ወደ ሔላም ሄደ፤ ሶርያውያንም በሰልፍ ወጥተው በዳዊት ላይ ጦርነት ከፈቱ፤ See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም17 ዳዊት ይህን በሰማ ጊዜ፣ መላውን እስራኤልን ሰብስቦ፤ ዮርዳኖስን ተሻግሮ ወደ ኤላም ሄደ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 ለዳዊት ይህ በተነገረው ጊዜ፥ መላውን እስራኤልን ሰበሰበ፤ ከዚያም ዮርዳኖስን ተሻግሮ ወደ ዔላም ሄደ። ሶርያውያንም ለጦርነት ተሰልፈው ዳዊትን በግንባር ገጠሙት፤ See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 ለዳዊትም ነገሩት፤ እስራኤልንም ሁሉ ሰበሰበ፤ ዮርዳኖስንም ተሻግሮ ወደ ኤላም መጣ፤ ሶርያውያንም በዳዊት ፊት ተሰልፈው ከእርሱ ጋር ተዋጉ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 ዳዊትም በሰማ ጊዜ እስራኤልን ሁሉ ሰበሰበ፥ ዮርዳኖስንም ተሻግሮ ወደ ኤላም መጣ፥ ሶርያውያንም በዳዊት ፊት ተሰልፈው ከእርሱ ጋር ተዋጉ። See the chapter |