Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ነገሥት 8:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ከሰባቱም የራብ ዓመቶች ፍጻሜ በኋላ ወደ እስራኤል ተመለሰች፤ መኖሪያ ቤትዋና የእርሻ መሬትዋ እንዲመለስላት ለመጠየቅ ወደ ንጉሡ ቀረበች።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ከሰባት ዓመት በኋላም፣ ከፍልስጥኤም ምድር ተመልሳ መጣች፤ ስለ ቤቷና ስለ መሬቷ አቤቱታ ለማቅረብም ወደ ንጉሡ ሄደች።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ከሰባቱም የራብ ዓመቶች ፍጻሜ በኋላ ወደ እስራኤል ተመለሰች፤ መኖሪያ ቤትዋና የእርሻ መሬትዋ እንዲመለስላት ለመጠየቅ ወደ ንጉሡ ቀረበች።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ሰባ​ቱም ዓመት ካለፈ በኋላ ያች ሴት ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ሀገር ተመ​ለ​ሰች፤ ሄዳም ስለ ቤቷና ስለ መሬቷ ልት​ጮህ ወደ ንጉሡ ወጣች።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ሰባቱም ዓመት በተፈጸመ ጊዜ ሴቲቱ ከፍልስጥኤም አገር ተመለሰች፤ ስለ ቤትዋና ስለ መሬትዋ ልትጮኽ ወደ ንጉሡ ወጣች።

See the chapter Copy




2 ነገሥት 8:3
10 Cross References  

ለድኾች በቅንነት ስለሚፈርድ፥ ሁሉ ነገር ይሳካለት ነበር፤ እግዚአብሔርን ማወቅ ይሉሃል ይህ ነው።


ግያዝ ለንጉሡ የሰጠውን መልስ ሴትዮዋ ለንጉሡ እውነት መሆኑን አረጋገጠችለት፤ ስለዚህም ንጉሡ አንድ ባለሥልጣን ጠርቶ፥ የእርስዋ የሆነው ማናቸውም ነገርና እንዲሁም የእርሻ መሬትዋ በሰባት ዓመት ጊዜ ውስጥ ያስገኘው የእህል ሰብል ጭምር እንዲመለስላት ትእዛዝ ሰጠላት።


አንድ ቀን የእስራኤል ንጉሥ በከተማይቱ የቅጽር ግንብ ላይ በሚመላለስበት ጊዜ አንዲት ሴት ድምፅዋን ከፍ አድርጋ “ንጉሥ ሆይ፥ እባክህ እርዳኝ!” ስትል ጮኸች።


ግያዝ “ለእኛ ስላደረገችው መልካም ነገር ሁሉ ምን አደርግላት ዘንድ እንደምትፈልግ ጠይቃት፤ ምናልባት ወደ ንጉሡ ወይም ወደ ጦር አዛዡ ዘንድ ሄጄ የምነግርላት ጉዳይ ሊኖር ይችላል” አለው። እርስዋም “በዘመዶች መካከል በምኖርበት በዚህ ስፍራ ምንም የሚቸግረኝ ነገር የለም” ስትል መለሰችለት።


ሴቲቱም ወደ ንጉሡ ቀርባ ወደ መሬት ለጥ ብላ እጅ ነሣችና “ንጉሥ ሆይ! እባክህ እርዳኝ!” አለችው።


ስለዚህም የኤልሳዕን ምክር ሰምታ ከነቤተሰብዋ ወደ ፍልስጥኤም አገር በመሰደድ እስከ ሰባት ዓመት ቈየች።


ንጉሡንም የኤልሳዕ አገልጋይ ከሆነው ከግያዝ ጋር ሲነጋገር አገኘችው፤ ንጉሡ ከግያዝ ጋር የሚነጋገረውም ኤልሳዕ ስላደረጋቸው ተአምራት ለማወቅ ፈልጎ ነበር፤


ወደ ይሁዳ አገር ለመሄድም አብረው መጓዝ ጀመሩ፤ ነገር ግን በመንገድ ላይ ሳሉ፥


Follow us:

Advertisements


Advertisements