Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ነገሥት 6:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 “ከእኛ መካከል ከእስራኤል ንጉሥ ጋር ግኑኝነት ያለው ማን እንደ ሆነ አትነግሩኝምን?” ሲል ጠየቃቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ይህም የሶርያን ንጉሥ እጅግ ስላበሳጨው፣ የጦር አለቆቹን ጠርቶ፣ “ከመካከላችን ከእስራኤል ንጉሥ ጋራ የተወዳጀ እንዳለ ለምን አትነግሩኝም?” ሲል ጠየቃቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 “ከእኛ መካከል ከእስራኤል ንጉሥ ጋር ግኑኝነት ያለው ማን እንደሆነ አትነግሩኝምን?” ሲል ጠየቃቸው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 የሶ​ር​ያም ንጉሥ መን​ፈስ ስለ​ዚህ እጅግ ተበ​ሳ​ጨች፤ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹ​ንም ጠርቶ፥ “ለእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ማን እን​ደ​ሚ​ነ​ግ​ረው አት​ነ​ግ​ሩ​ኝ​ምን?” አላ​ቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 የሶርያም ንጉሥ ልብ ስለዚህ እጅግ ታወከ፤ ባሪያዎቹንም ጠርቶ “ከእኛ ዘንድ ከእስራኤል ንጉሥ ጋር የተወዳጀ እንዳለ አትነግሩኝምን?” አላቸው።

See the chapter Copy




2 ነገሥት 6:11
8 Cross References  

ሴቲቱም ወደ ሳኦል መጥታ ሲንቀጠቀጥ ስላየችው እንዲህ አለችው፦ “እኔ አገልጋይህ የአንተን ቃል ሰምቼ ሕይወቴን እስከ ማሳለፍ ደርሼአለሁ፤ ያልከኝንም ነገር አዳመጥኩ፤


በእኔስ ላይ ሤራ የምታካሄዱት ስለዚህ ነውን? የገዛ ልጄ ከእሴይ ልጅ ጋር መተባበሩን የነገረኝ ከእናንተ አንድ እንኳ የለም፤ ስለ እኔ የሚያስብ ከቶ ማንም የለም፤ ወይም ዛሬ እንደሚያደርገው ሁሉ አገልጋዬ በእኔ ላይ እንዲሸምቅ ልጄ ያነሣሣው መሆኑን ከእናንተ ማንም የነገረኝ የለም።”


ስለዚህም የእስራኤል ንጉሥ በዚያ የሚኖሩትን ወታደሮቹን ስላስጠነቀቃቸው ነቅተው ይጠባበቁ ነበር፤ ይህም ድርጊት ብዙ ጊዜ በተደጋጋሚ ተፈጸመ።


ከእነርሱም አንዱ “ንጉሥ ሆይ፥ ከእኛ መካከል ይህን የሚያደርግ ማንም የለም፤ በመኝታ ክፍልህ እንኳ ሆነህ የምትናገረውን ሁሉ ሳይቀር ለእስራኤል ንጉሥ ምሥጢሩን የሚገልጥለት ኤልሳዕ የተባለው ነቢይ ነው” ሲል መለሰለት።


Follow us:

Advertisements


Advertisements