Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ነገሥት 3:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ምንም ዝናብና ነፋስ ባታዩም፥ ይህ ሸለቆ በውሃ የተሞላ ይሆናል፤ እናንተ፥ የቀንድ ከብቶቻችሁና የጭነት እንስሶቻችሁ ሁሉ የምትጠጡት በቂ ውሃ ታገኛላችሁ።’

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ ‘ነፋስም ሆነ ዝናብ አታዩም፤ ሸለቆው ግን በውሃ ይሞላል፤ እናንተ፣ የቀንድ ከብቶቻችሁና ሌሎች እንስሶቻችሁም ትጠጣላችሁ።’

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ምንም ዝናብና ነፋስ ባታዩም፥ ይህ ሸለቆ በውሃ የተሞላ ይሆናል፤ እናንተ፥ የቀንድ ከብቶቻችሁና የጭነት እንስሶቻችሁ ሁሉ የምትጠጡት በቂ ውሃ ታገኛላችሁ።’

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ ይላል፦ ነፋስ አታ​ዩም፤ ዝና​ብም አታ​ዩም፤ ይህ ሸለቆ ግን ውኃ ይሞ​ላል፤ እና​ን​ተም፥ ከብ​ቶ​ቻ​ች​ሁም፥ እን​ስ​ሶ​ቻ​ች​ሁም፥ ትጠ​ጣ​ላ​ችሁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ‘ነፋስ አታዩም፤ ዝናብም አታዩም፤ ይህ ሸለቆ ግን ውሃ ይሞላል፤ እናንተም ከብቶቻችሁም እንስሶቻችሁም ትጠጣላችሁ።’

See the chapter Copy




2 ነገሥት 3:17
9 Cross References  

እንደገናም በበረሓው ብዙ ኲሬዎች እንዲኖሩ፥ በደረቁም ምድር ብዙ ምንጮች እንዲገኙ አደረገ።


እግዚአብሔር በምድረ በዳ በመራቸው ጊዜ ውሃ አልጠማቸውም፤ ይልቁንስ ውሃ ከአለት እንዲፈልቅላቸው አደረገ። አለቱን ከፍሎ ውሃ አጐረፈላቸው።


ባካ በተባለው ደረቅ ሸለቆ በሚያልፉበት ጊዜ እግዚአብሔር ምንጭን ያፈልቅላቸዋል፤ የበልግም ዝናብ ኩሬዎችን ይሞላቸዋል።


እነሆ፥ እኔ በሲና ተራራ በአለት ላይ በፊትህ እቆማለሁ፤ አንተም አለቱን ምታው፤ ሕዝቡም የሚጠጡት ውሃ ከውስጡ ይፈልቃል፤” ሙሴም በእስራኤል አለቆች ፊት እንደዚሁ አደረገ።


“እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ‘በዚህ የደረቀ ሸለቆ ሁሉ የውሃ ጒድጓድ ቆፍሩ፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements