Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ነገሥት 16:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 አካዝም ከደማስቆ በተመለሰ ጊዜ ያ መሠዊያ በትክክል መሠራቱን ለማየትና መሥዋዕት ለማቅረብ ወደ መሠዊያው ወጣ፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ንጉሡ ከደማስቆ ተመልሶ በመጣ ጊዜ፣ መሠዊያውን አየ፤ ቀርቦም በመሠዊያው ላይ ወጣ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 አካዝም ከደማስቆ በተመለሰ ጊዜ ያ መሠዊያ በትክክል መሠራቱን ለማየትና መሥዋዕት ለማቅረብ ወደ መሠዊያው ወጣ፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ንጉ​ሡም ከደ​ማ​ስቆ በመጣ ጊዜ መሠ​ዊ​ያ​ውን አየ፤ ንጉ​ሡም ወደ መሠ​ዊ​ያው ወጣ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ንጉሡም ከደማስቆ በመጣ ጊዜ መሠዊያውን አየ፤ ንጉሡም ወደ መሠዊያው ቀርቦ በእርሱ ላይ ወጣ።

See the chapter Copy




2 ነገሥት 16:12
8 Cross References  

በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ለባዕዳን አማልክት ዕጣን የሚታጠንባቸውን የኰረብታ የማምለኪያ ስፍራዎችን ሠራ፤ በዚህም ሁኔታ አካዝ የቀድሞ አባቶቹን አምላክ የእግዚአብሔርን ቊጣ በራሱ ላይ አመጣ።


አካዝ ድልን ላጐናጸፉአቸው ለሶርያውያን አማልክት መሥዋዕት አቀረበ፤ ይህንንም ያደረገበት ምክንያት “የሶርያ አማልክት የሶርያን ነገሥታት ረድተዋል፤ መሥዋዕት ባቀርብላቸው እኔንም ይረዱኛል” ብሎ በማሰብ ነው፤ ይህም ድርጊት በራሱና በሀገሩ ላይ ጥፋትን አመጣ፤


ኢዮርብዓም መሥዋዕት ለማቅረብ በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ ሳለ በእግዚአብሔር ትእዛዝ የተላከ አንድ ነቢይ እነሆ ከይሁዳ መጥቶ እዚያ ደረሰ፤


ስለዚህም ኡሪያ ንጉሥ አካዝ ተመልሶ ከመምጣቱ በፊት ልክ ያንኑ የሚመስል መሠዊያ ሠራ፤


እንዲሁም በዚያ መሠዊያ ላይ የሚቃጠል የእንስሶች መሥዋዕትና የእህል መባ አቀረበ፤ የመባውን ወይን ጠጅና የኅብረት መሥዋዕት ደም አፈሰሰበት።


በዓል እንዲሆን እርሱ ራሱ በወሰነው ስምንተኛ ወር በገባ በዐሥራ አምስተኛው ቀን ወደ ቤትኤል ሄደ፤ በዚያም ለእስራኤል በወሰነላቸው መሠረት በዓል ለማክበር በመሠዊያው ላይ መሥዋዕት አቀረበ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements