Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ነገሥት 10:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ከንጉሡ ተወላጆች የተሻለውን አንዱን መርጣችሁ አንግሡት፤ ለእርሱም በመከላከል ተዋጉለት!” የሚል ነበር።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ከጌታችሁ ልጆች መካከል ብልጫ ያለውንና ተገቢ ነው የምትሉትን መርጣችሁ በአባቱ ዙፋን አስቀምጡት። ከዚያም ስለ ጌታችሁ ቤት ተዋጉ።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ከንጉሡ ተወላጆች የተሻለውን አንዱን መርጣችሁ አንግሡት፤ ለእርሱም በመከላከል ተዋጉለት!” የሚል ነበር።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ከጌ​ታ​ችሁ ልጆች ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኛ​ች​ሁ​ንና የሚ​ሻ​ላ​ች​ሁን ምረጡ፤ በአ​ባ​ቱም ዙፋን አስ​ቀ​ም​ጡት፤ ስለ ጌታ​ች​ሁም ቤት ተዋጉ።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ከጌታችሁ ልጆች ደስ የሚያሰኛችሁንና የሚሻላችሁን ምረጡ፤ በአባቱም ዙፋን አስቀምጡት፤ ስለ ጌታችሁም ቤት ተዋጉ፤” ብሎ ወደ ሰማርያ ሰደደ፤

See the chapter Copy




2 ነገሥት 10:3
10 Cross References  

ኢየሱስ “የእኔ መንግሥት ከዚህ ዓለም አይደለችም፤ መንግሥቴ ከዚህ ዓለም ብትሆን ኖሮ በአይሁድ ባለሥልጣኖች እጅ እንዳልወድቅ ሎሌዎቼ በተዋጉልኝ ነበር፤ መንግሥቴ ግን ከዚህ ዓለም አይደለችም” ሲል መለሰ።


ሕዝቡም ሁሉ ወደ ጌልጌላ ሄደው በእግዚአብሔር ፊት የሳኦልን ንጉሥነት አጸደቁ፤ በእግዚአብሔርም ፊት የአንድነት መሥዋዕት አቀረቡ፤ በዓሉንም ሳኦልና መላው ሕዝብ በታላቅ ደስታ አከበሩት።


ሳሙኤልም ሕዝቡን “እግዚአብሔር የመረጠው ሰው እነሆ ይህ ነው! ከእኛም መካከል እርሱን የሚስተካከለው የለም” አለ። ሕዝቡም ሁሉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው “ረጅም ዕድሜ ለንጉሡ ይሁን!” አሉ።


“እናንተ ለንጉሡ ተወላጆች ኀላፊዎች ናችሁ፤ ፈረሶችና ሠረገሎች የጦር መሣሪያዎችና የተመሸጉ ከተሞች ሁሉ በእናንተ እጅ ይገኛሉ፤ እንግዲህ ይህ ደብዳቤ እንደ ደረሳችሁ ወዲያውኑ፥


ከዚህም የተነሣ የሰማርያ ገዢዎች በፍርሃት ተሸብረው፥ “ንጉሥ ኢዮራምና ንጉሥ አካዝያስ ሊቋቋሙ ያልቻሉትን እኛ እንዴት ኢዩን ልንቋቋመው እንችላለን?” አሉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements