Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ነገሥት 10:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ከዚህም በኋላ ኢዩ የተቀደሱ አባላት ኀላፊ የሆነውን ካህን አልባሳቱን ሁሉ አውጥቶ ለባዓል አምላኪዎች ያጐናጽፋቸው ዘንድ አዘዘ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ኢዩም የልብስ ቤቱን ኀላፊ፣ “ለበኣል አገልጋዮች ሁሉ አልባሳት አውጣ” አለው፤ እርሱም አልባሳቱን አወጣላቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ከዚህም በኋላ ኢዩ የተቀደሱ አባላት ኃላፊ የሆነውን ካህን አልባሳቱን ሁሉ አውጥቶ ለበዓል አምላኪዎች ያጐናጽፋቸው ዘንድ አዘዘ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 የዕቃ ቤቱ​ንም ሹም፥ “ለበ​ዓል አገ​ል​ጋ​ዮች ሁሉ ልብ​ስን አውጣ” አለው። የሚ​ያ​ለ​ብ​ሳ​ቸ​ው​ንም ልብ​ሱን አወ​ጣ​ላ​ቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ዕቃ ቤቱንም “ለበኣል አገልጋዮች ሁሉ ልብስ አውጣ፤” አለው። ልብሱንም አወጣላቸው።

See the chapter Copy




2 ነገሥት 10:22
4 Cross References  

ለክብርና ለውበት ይሆነው ዘንድ ለወንድምህ ለአሮን የክህነት ልብስ ሥራለት።


ኢዩም በእስራኤል ምድር ሁሉ መልእክት አስተላለፈ፤ ባዓልን የሚያመልኩ ሁሉ ተሰበሰቡ፤ አንድም እንኳ የቀረ ሰው አልነበረም፤ ሁሉም ወደ ባዓል ቤተ መቅደስ ገብተው ዳር እስከ ዳር ሞሉት፤


ከዚህም በኋላ ኢዩ ራሱ የሬካብ ልጅ ከሆነው ከኢዮናዳብ ጋር አብሮ ወደ ቤተ መቅደሱ ገባ፤ በዚያም ለሕዝቡ “እንግዲህ በዚህ የሚገኙት የባዓል አምላኪዎች ብቻ መሆናቸውንና እግዚአብሔርን የሚያመልክ አንድም አለመኖሩን በሚገባ አረጋግጡ” ሲል ተናገረ፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements