Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 9:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ወደ ከተማይቱም ዳርቻ በደረሱ ጊዜ ሳሙኤል ሳኦልን “አገልጋይህ ቀድሞን ወደ ፊት እንዲሄድ ንገረው” አለው፤ አገልጋዩም ቀድሞ ከሄደ በኋላ ሳሙኤል ሳኦልን እንደገና “አንተ እዚህ ትንሽ ቈይ፤ እኔም እግዚአብሔር ያለውን ሁሉ እነግርሃለሁ” አለው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ወደ ከተማዪቱ ዳርቻ እየወረዱ ሳለ፣ ሳሙኤል ሳኦልን፣ “አገልጋይህ ወደ ፊት ቀድሞን እንዲሄድ ንገረው” አለው፤ አገልጋዩም እንደ ተነገረው አደረገ፤ ከዚህ በኋላ ሳሙኤል፣ “አንተ ግን ከእግዚአብሔር የተላከ መልእክት እነግርህ ዘንድ ለጥቂት ጊዜ እዚህ ቈይ” አለው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ወደ ከተማዪቱ ዳርቻ እየወረዱ ሳለ፥ ሳሙኤል ሳኦልን፥ “አገልጋይህ ወደ ፊት ቀድሞን እንዲሄድ ንገረው፤ አገልጋይህም እንዳለፈ፥ አንተ ግን ከጌታ የተላከ መልእክት እንድነግርህ ለጥቂት ጊዜ እዚህ ቆይ” አለው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 እነ​ር​ሱም በከ​ተ​ማ​ዪቱ ዳር ሲወ​ርዱ ሳሙ​ኤል ሳኦ​ልን፥ “ብላ​ቴ​ናው ወደ ፊታ​ችን እን​ዲ​ያ​ልፍ እዘ​ዘው፤ አንተ ግን ከእኔ ጋር ከዚህ ቁምና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስማ” አለው። ብላ​ቴ​ና​ውም አለፈ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 እነርሱም በከተማይቱ ዳር ሲወርዱ ሳሙኤል ሳኦልን፦ ብላቴናውን ወደ ፊታችን እንዲያልፍ እዘዘው፥ አንተ ግን የእግዚአብሔርን ቃል አሰማህ ዘንድ በዚህ ቁም አለው። ብላቴናውም አለፈ።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 9:27
7 Cross References  

ሳሙኤልም “ተወው በቃ፤ እግዚአብሔር ትናንትና ማታ የገለጠልኝን እነግርሃለሁ” አለው። ሳኦልም “እሺ ንገረኝ” አለ።


በነጋም ጊዜ ማለዳ ሳሙኤል ከሰገነቱ ላይ ሳኦልን ጠርቶ “እንግዲህ ተነሥ፤ ላሰናብትህና መንገድህን ቀጥል” አለው፤ ሳኦልም ከመኝታው ተነሣ፤ እርሱና ሳሙኤልም አብረው ወደ መንገዱ ሄዱ፤


ሳሙኤል የወይራ ዘይት መያዣውን ቀንድ ወስዶ በሳኦል ራስ ላይ አፈሰሰው፤ ሳመውም። ከዚያም በኋላ “እግዚአብሔር በሕዝቡ በእስራኤል ላይ መሪ እንድትሆን ቀባህ፤ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ነግሠህ በዙሪያቸው ካሉ ጠላቶች ታድናቸዋለህ እግዚአብሔር በርስቱ ላይ የሾመህ ለመሆኑ ይህ ማስረጃ ነው፤


ኢሳይያስም ንጉሡን እንዲህ አለው፦ “ሁሉን የሚችል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦


Follow us:

Advertisements


Advertisements