1 ሳሙኤል 5:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 እንደገና ወደ ፍልስጥኤማውያን ነገሥታት ሁሉ መልእክተኞች ልከው “እኛንና ቤተሰባችንን ሁሉ ከመፍጀቱ በፊት የእስራኤልን የቃል ኪዳን ታቦት ወደ ስፍራው መልሳችሁ ላኩ” አሉ፤ እግዚአብሔር በብርቱ ስለ ቀጣቸው በመላ ከተማይቱ የሚያስጨንቅ የሞት ፍርሀት ነበር፤ See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም11 የእግዚአብሔር እጅ በርትቶባቸው ስለ ነበር፣ ሞት ከተማዪቱን እጅግ አስደንግጧት ነበርና ሕዝቡ የፍልስጥኤማውያንን ገዦች በሙሉ ጠርተው፣ “የእስራኤልን አምላክ ታቦት ከዚህ አርቁልን፤ ወደ ገዛ ስፍራው ይመለስ፤ አለዚያ እኛንም ሕዝባችንንም ይፈጃል” አሉ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 የእግዚአብሔር እጅ በርትቶባቸው ስለ ነበር፥ ሞት ከተማዪቱን እጅግ አስደንግጧት ነበርና ሕዝቡ የፍልስጥኤማውያንን ገዢዎች በሙሉ ጠርተው፥ “የእስራኤልን አምላክ ታቦት ከዚህ አርቁልን፤ ወደ ገዛ ስፍራው ይመለስ፤ ያለበለዚያ እኛንም ሕዝባችንንም ይፈጃል” አሉ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 ልከውም የፍልስጥኤማውያንን አለቆች ሁሉ ሰብስበው፥ “የእስራኤልን አምላክ ታቦት ስደዱአት፤ እኛንና ሕዝባችንን እንዳትገድል በስፍራዋ ትቀመጥ” አሉ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 በከተማይቱ ሁሉ የሞት ድንጋጤ ነበርና፥ የእግዚአብሔርም እጅ በዚያ እጅግ ከብዳ ነበረችና ልከው የፍልስጥኤማውያንን አለቆች ሁሉ ሰብስበው፦ የእስራኤልን አምላክ ታቦት ስደዱ፥ እኛንና ሕዝባችንን እንዳይገድል ወደ ስፍራው ይመለስ አሉ። See the chapter |