1 ሳሙኤል 4:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 ከጦርነት የተረፉት ወደ ሰፈራቸው በተመለሱ ጊዜ የእስራኤል መሪዎች እንዲህ አሉ፤ “ዛሬ ፍልስጥኤማውያን እኛን ድል ያደርጉ ዘንድ እግዚአብሔር ስለምን ፈቀደላቸው? ከእኛ ጋር በመሄድ ከጠላቶቻችን እጅ ያድነን ዘንድ እንግዲህ እንሂድና የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ከሴሎ እናምጣ።” See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም3 ሰራዊቱ ወደ ሰፈር በተመለሰ ጊዜ የእስራኤል አለቆች፣ “ዛሬ እግዚአብሔር በፍልስጥኤማውያን እንድንሸነፍ ያደረገን ለምንድን ነው? ዐብሮን እንዲወጣ፣ ከጠላቶቻችንም እጅ እንዲያድነን የእግዚአብሔርን የኪዳኑን ታቦት ከሴሎ እናምጣ” አሉ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 ሠራዊቱ ወደ ሰፈር በተመለሰ ጊዜ የእስራኤል አለቆች፥ “ዛሬ ጌታ በፍልስጥኤማውያን እንድንሸነፍ ያደረገን ለምንድን ነው? አብሮን እንዲወጣ፥ ከጠላቶቻችንም እጅ እንዲያድነን የጌታን የኪዳኑን ታቦት ከሴሎ እናምጣ” አሉ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 ሕዝቡም ወደ ሰፈር በተመለሱ ጊዜ የእስራኤል ሽማግሌዎች፥ “ዛሬ እግዚአብሔር በፍልስጥኤማውያን ፊት ስለምን ጣለን? በፊታችን እንድትሄድ፥ ከጠላቶቻችንም እጅ እንድታድነን፥ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳኑን ታቦት ከሴሎ እናምጣ” አሉ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 ሕዝቡም ወደ ሰፈር በመጡ ጊዜ የእስራኤል ሽማግሌዎች፦ ዛሬ እግዚአብሔር በፍልስጥኤማውያን ፊት ስለ ምን መታን? በመካከላችን እንዲሄድ፥ ከጠላቶቻችንም እጅ እንዲያድነን፥ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳኑን ታቦት ከሴሎ እናምጣ አሉ። See the chapter |