1 ሳሙኤል 4:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 ፍልስጥኤማውያንም አደጋ መጣል ጀመሩ፤ ከከባድ ጦርነት በኋላ እስራኤላውያንን ድል በመንሣት በጦር ሜዳ አራት ሺህ ሰው ገደሉባቸው፤ See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም2 ፍልስጥኤማውያን እስራኤልን ለመግጠም ሰራዊታቸውን አሰለፉ፤ ጦርነቱ እንደ ተፋፋመም፣ እስራኤላውያን በፍልስጥኤማውያን ተሸነፉ፤ በጦርነቱም ላይ አራት ሺሕ ያህል እስራኤላውያን ተገደሉ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 ፍልስጥኤማውያን እስራኤልን ለመግጠም ሠራዊታቸውን አሰለፉ፤ ጦርነቱ እንደ ተፋፋመም፥ እስራኤላውያን በፍልስጥኤማውያን ተሸነፉ፤ በጦርነቱም ላይ አራት ሺህ ያህል እስራኤላውያን ተገደሉ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 ፍልስጥኤማውያንም እስራኤልን ለመውጋት ተሰለፉ፤ እስራኤልም ሸሹ፤ በፍልስጥኤማውያንም ፊት ድል ሆኑ፤ ጦርነት በተደረገበትም ስፍራ ከእስራኤል አራት ሺህ ሰዎች ተገደሉ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 ፍልስጥኤማውያንም በእስራኤል ላይ ተሰለፉ፥ ሰልፋም በተመደበ ጊዜ እስራኤል በፍልስጥኤማውያን ፊት ተመቱ፥ ጦርነት በተደረገበትም ስፍራ ከእስራኤል አራት ሺህ የሚያህሉ ሰዎችን ገደሉ። See the chapter |