1 ሳሙኤል 31:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 ጀግኖቻቸው በድንገት ተነሥተው በመገሥገሥ በሌሊት ወደ ቤትሻን ሄዱ፤ የሳኦልንና የልጆቹን አስከሬን ከከተማይቱ ቅጽር ግንብ ላይ አውርደው ወደ ያቤሽ በማምጣት አቃጠሉአቸው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም12 ጀግኖቻቸው ሁሉ ተነሥተው ሌሊቱን ሙሉ ተጓዙ፤ የሳኦልንና የልጆቹን ሬሳ ከቤትሳን ግንብ ላይ አውርደው ወደ ኢያቢስ አምጥተው አቃጠሉ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 ጀግኖቻቸው ሁሉ በሌሊት ወደ ቤትሻን ሄዱ። የሳኦልንና የልጆቹንም ሬሳ ከግንቡ ላይ አውርደው ወደ ያቤሽ አምጥተው አቃጠሉ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 የሳኦልንም ሬሳ፥ የልጁ የዮናታንንም ሬሳ ከቤትሶም ቅጥር ላይ አወረዱ፤ ወደ ኢያቢስም አመጡአቸው፤ በዚያም አቃጠሉአቸው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 ጀግኖች ሰዎች ሁሉ ተነሥተው ሌሊቱን ሁሉ ሄዱ፥ የሳኦልንም ሬሳ የልጆቹንም ሬሳ ከቤትሳን ቅጥር ላይ አወረዱ፥ ወደ ኢያቢስም መጡ፥ በዚያም አቃጠሉት። See the chapter |