1 ሳሙኤል 3:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 እግዚአብሔርም እንደገና ለሦስተኛ ጊዜ ሳሙኤልን ጠራው፤ ሳሙኤልም ተነሥቶ ወደ ዔሊ በመሄድ “እነሆ! ስለጠራኸኝ መጥቻለሁ” አለው። ከዚህም በኋላ ሳሙኤልን ይጠራው የነበረው እግዚአብሔር መሆኑን ዔሊ ተገነዘበ፤ See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም8 እግዚአብሔር ሳሙኤልን ለሦስተኛ ጊዜ ጠራው፤ አሁንም ሳሙኤል ተነሥቶ ወደ ዔሊ በመሄድ፣ “እነሆኝ የጠራኸኝ” አለው። ዔሊ በዚህ ጊዜ ብላቴናውን ይጠራ የነበረው እግዚአብሔር መሆኑን ተረዳ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 ጌታም ሳሙኤልን ለሦስተኛ ጊዜ ጠራው፤ አሁንም ሳሙኤል ተነሥቶ ወደ ዔሊ በመሄድ፥ “ስለ ጠራኸኝ እነሆ! መጥቻለሁ” አለው። ዔሊም በዚህ ጊዜ ሳሙኤልን ይጠራ የነበረው ጌታ መሆኑን ተረዳ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 እግዚአብሔርም ሳሙኤልን እንደ ገና ሦስተኛ ጊዜ ጠራው። እርሱም ተነሥቶ ወደ ዔሊ ሄደና፥ “እነሆኝ ስለ ጠራኸኝ መጣሁ” አለ። ዔሊም እግዚአብሔር ልጁን እንደ ጠራው አስተዋለ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 እግዚአብሔርም ሳሙኤልን እንደ ገና ሦስተኛ ጊዜ ጠራው። እርሱም ተነሥቶ ወደ ዔሊ ሄደና፦ እነሆኝ የጠራኽኝ አለ። ዔሊም እግዚአብሔር ብላቴናውን እንደ ጠራው አስተዋለ። See the chapter |