Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 3:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ሳሙኤልም እስኪነጋ ድረስ ተኝቶ ቈየ፤ በነጋም ጊዜ ተነሥቶ የእግዚአብሔርን ቤት በሮች ከፈተ፤ ያየውንም ራእይ ለዔሊ ለመንገር ፈራ፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ሳሙኤል እስኪነጋ ድረስ ተኛ፤ ከዚያም ተነሥቶ የእግዚአብሔርን ቤት በሮች ከፈተ፤ ራእዩንም ለዔሊ መንገር ፈራ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ሳሙኤል እስኪ ነጋ ድረስ ተኛ፤ ከዚያም ተነሥቶ የጌታን ቤት በሮች ከፈተ፤ ራእዩንም ለዔሊ መንገር ፈራ፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ሳሙ​ኤ​ልም እስ​ኪ​ነጋ ተኛ፥ ማል​ዶም ተነ​ሥቶ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ደጅ ከፈተ። ሳሙ​ኤ​ልም ራእ​ዩን ለዔሊ መን​ገር ፈራ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ሳሙኤልም እስኪነጋ ተኛ፥ ማልዶም ተነሥቶ የእግዚአብሔርን ቤት ደጅ ከፈተ። ሳሙኤልም ራእዩን ለዔሊ መንገር ፈራ።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 3:15
8 Cross References  

የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “በመሠዊያዬ ላይ ከንቱ እሳትን ከምታቃጥሉበት ይልቅ የቤተ መቅደሱን በር የሚዘጋ ምነው ከእናንተ አንድ ሰው እንኳ በተገኘ! በእናንተ ደስ ስለማይለኝ ለእኔ የምታቀርቡትን ቊርባን አልቀበልም፤


አንድ ቀን በሴሎ መሥዋዕት ሠውተው ከበሉና ከጠጡ በኋላ ሐና ተነሣች፤ ካህኑም ዔሊ በእግዚአብሔር መቅደስ በር አጠገብ ተቀምጦ ነበር።


እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፤ “እነሆ፥ እኔ የምነግራችሁን አድምጡ! በመካከላችሁ ነቢያት ቢኖሩ ራሴን የምገልጥላቸው በራእይ ነው፤ በሕልምም አነጋግራቸዋለሁ፤


እግዚአብሔርም መጥቶ በዚያ ቆመ፤ ከዚያም በፊት ያደርግ በነበረው ዐይነት “ሳሙኤል! ሳሙኤል!” ብሎ ጠራው። ሳሙኤልም “ጌታ ሆይ! እነሆ አገልጋይህ እሰማለሁና ተናገር” አለው።


ዔሊ ግን ሳሙኤልን “ልጄ ሳሙኤል ሆይ!” ሲል ጠራው። ሳሙኤልም “እነሆ አለሁ ጌታዬ!” ሲል መለሰ።


በራክያ፥ ኤልቃና፥ ዖቤድኤዶምና ዩሒያ የቃል ኪዳኑ ታቦት ጠባቂዎች ሆነው ተመረጡ፤ ካህናቱ ሸባንያ፥ ኢዮሣፍጥ፥ ናትናኤል፥ ዐማሣይ፥ ዘካርያስ፥ በናያና ኤሊዔዘር በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ፊት እየሄዱ እምቢልታ እንዲነፉ ተመረጡ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements