1 ሳሙኤል 27:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 ወንዶችንም ሴቶችንም ሁሉ እየገደለ፥ በጎችን የቀንድ ከብቶችን፥ አህዮችን፥ ግመሎችንና ልብሱንም ሁሉ ይወስድ ነበር፤ ከዚያም በኋላ ዳዊት ወደ አኪሽ ተመለሰ፤ See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 ዳዊትም ምድሪቱን በመታበት ጊዜ፣ ወንድም ሆነ ሴት በሕይወት አላስቀረም፤ ነገር ግን በጎችንና ላሞችን፣ አህዮችንና ግመሎችን እንዲሁም ልብሶችን ወሰደ፤ ወደ አንኩስም ተመለሰ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 ዳዊትም ምድሪቱን በመታበት ጊዜ፥ ወንድም ሆነ ሴት በሕይወት አላስቀረም፤ በጎችንና ላሞችን፥ አህዮችንና ግመሎችን እንዲሁም ልብሶችን ወሰደ፤ ወደ አኪሽም ይዞ ተመለሰ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 ዳዊትም ሀገሪቱን መታ፤ ወንድም ሆነ፥ ሴትም ሆነ፥ ማንንም በሕይወት አልተወም፤ በጎችንና ላሞችን፥ አህያዎችንና ግመሎችን፥ ልብስንም ማረከ፤ ተመልሶም ወደ አንኩስ መጣ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 ዳዊትም ምድሪቱን መታ፥ ወንድ ሆነ ሴትም ሆነ ማንንም በሕይወት አልተወም፥ በጎችንና ላሞችን አህያዎችንና ግመሎችን ልብስንም ማረከ፥ ተመልሶም ወደ አንኩስ መጣ። See the chapter |