Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 26:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ሳኦልም ዳዊትን “ልጄ ሆይ፥ እግዚአብሔር ይባርክህ! ብዙ ነገርን ታደርጋለህ፤ ይሳካልሃልም” አለው። ስለዚህም ዳዊት ወደ ፈለገበት ቦታ ሄደ፤ ሳኦልም ወደ ቤቱ ተመለሰ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ከዚያም ሳኦል ዳዊትን፣ “ልጄ ዳዊት ሆይ፤ የተባረክህ ሁን፤ ታላቅ ነገር ታደርጋለህ፤ በርግጥም ይከናወንልሃል” አለው። ስለዚህም ዳዊት ወደሚሄድበት ሄደ፤ ሳኦልም ወደ ቤቱ ተመለሰ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ከዚያም ሳኦል ዳዊትን፥ “ልጄ ዳዊት ሆይ፤ የተባረክህ ሁን፤ ብዙ ነገር ታደርጋለህ፤ በእርግጥም ይከናወንልሃል” አለው። ስለዚህም ዳዊት ወደሚሄድበት ሄደ፤ ሳኦልም ወደ ስፍራው ተመለሰ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን፥ “ልጄ ዳዊት ሆይ! ቡሩክ ሁን፤ ማድ​ረ​ግን ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ መቻ​ል​ንም ትች​ላ​ለህ” አለው። ዳዊ​ትም መን​ገ​ዱን ሄደ፤ ሳኦ​ልም ወደ ስፍ​ራው ተመ​ለሰ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ሳኦል ዳዊትን፦ ልጄ ዳዊት ሆይ፥ ቡሩክ ሁን፥ ማድረግን ታደርጋለህ፥ መቻልንም ትችላለህ አለው። ዳዊትም መንገዱን ሄደ፥ ሳኦልም ወደ ሰፍራው ተመለሰ።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 26:25
10 Cross References  

እርሱም ልቡ በጥላቻ የተሞላ ስለ ሆነ፤ በሚያባብል ቃል ቢያቈላምጥህም አትመነው፤


ጠላት በእጁ ገብቶለት ጒዳት ሳያደርስበት የሚለቀው ሰው ከቶ የት ይገኛል? ዛሬ ለእኔ ስላደረግኸው መልካም ነገር እግዚአብሔር ይባርክህ!


ሰውየውም፥ “ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ ያዕቆብ አይባልም፤ ከእግዚአብሔርም ከሰውም ጋር ታግለህ አሸንፈሃል፤ ስለዚህ ስምህ ‘እስራኤል’ ይባላል” አለው።


እንግዲህ በወደደን በክርስቶስ እነዚህን ነገሮች ሁሉ ድል በመንሣት ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።


ከክርስቶስ ፍቅር ሊለየን የሚችል ማነው? ችግር ወይስ መከራ? ስደት፥ ወይስ ራብ? ወይስ ራቊትነት፥ ወይስ አደጋ? ወይስ ሰይፍ?


ከመልአኩም ጋር ታግሎ በረታ፤ አልቅሶም ምሕረትን ለመነ፤ ሌላ ጊዜም በቤትኤል የተገኘው እግዚአብሔር እኛን አነጋገረን።


አንቺን ለማጥፋት የሚሠራ መሣሪያ ዘላቂነት አይኖረውም፤ ለሚከሱሽ ሁሉ በቂ መልስ ይኖርሻል፤ የእኔ አገልጋዮች ርስትና ከእኔ የሚፈረድላቸው ፍርድ ይህ ነው፤” ይላል እግዚአብሔር።


ዳዊትም ይህን እንደሚያደርግ ማለለት። ከዚህ በኋላም ሳኦል ወደ ቤቱ ተመልሶ ሄደ፤ ዳዊትና ተከታዮቹም ወደሚሸሸጉበት ስፍራ ተመለሱ።


እነሆ፥ አንተ የእስራኤል ንጉሥ እንደምትሆንና የእስራኤልም መንግሥት በአንተ አገዛዝ ሥር ጸንቶ እንደሚኖር ዛሬ አረጋግጫለሁ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements