Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 26:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ድምፁንም ከፍ አድርጎ ወደ ሳኦል ወታደሮችና ወደ አበኔር በመጮኽ “አበኔር ሆይ! መልስ ስጠኝ” አለው። አበኔርም “እንዲህ እያልክ በንጉሡ ላይ የምትጮኽ አንተ ማነህ?” አለ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ዳዊት ሰራዊቱንና የኔርን ልጅ አብኔርን፣ “አበኔር ሆይ፣ አትመልስልኝምን?” ሲል ተጣራ። አበኔርም፣ “በንጉሡ ላይ የምትጮኽ አንተ ማነህ?” በማለት መለሰ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ዳዊት ሠራዊቱንና የኔርን ልጅ አቤኔርን፥ “አቤኔር ሆይ፥ አትመልስልኝምን?” ሲል ተጣራ። አቤኔርም፥ “በንጉሡ ላይ የምትጮኽ አንተ ማነህ?” በማለት መለሰ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ዳዊ​ትም ሕዝ​ቡ​ንና የኔር ልጅ አቤ​ኔ​ርን ጠራ​ቸው፥ “አቤ​ኔር ሆይ፥ አት​መ​ል​ስ​ምን?” አለው። አቤ​ኔ​ርም መልሶ፥ “አንተ የም​ት​ጠ​ራኝ ማን ነህ?” አለ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ዳዊትም ለሕዝቡና ለኔር ልጅ ለአበኔር፦ አበኔር ሆይ፥ አትመልስምን? ብሎ ጮኸ። አበኔርም መልሶ፦ ለንጉሡ የምትጮኸው አንተ ማን ነህ? አለ።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 26:14
4 Cross References  

ሚስቱም አሒኖዓም ተብላ የምትጠራ የአሒማዓጽ ልጅ ነበረች፤ የሠራዊቱም አዛዥ አበኔር ተብሎ የሚጠራው የአጐቱ የኔር ልጅ ነበር።


ከዚህ በኋላ ዳዊት ከሸለቆው ባሻገር ወደሚገኘው ቦታ ተሻገረ፤ ከእነርሱም ራቅ ብሎ በተራራው ጫፍ ላይ ቆመ።


ዳዊትም “አበኔር! አንተ በእስራኤል የታወቅህ ታላቅ ሰው አይደለህምን? ታዲያ ጌታህን ንጉሡን በደንብ የማትጠብቀው ስለምንድን ነው? እነሆ፥ ከእኛ አንድ ሰው ጌታህን ለመግደል ወደ ሰፈር ገብቶ ነበር፤


የሳኦል ሠራዊት አዛዥ የኔር ልጅ አበኔር ከሳኦል ልጅ ከኢያቡስቴ ጋር የዮርዳኖስን ወንዝ በመሻገር ወደ ማሕናይም ሸሽቶ ሄደ፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements