Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 23:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ሳኦልና ወታደሮቹም ዳዊትን ለማሳደድ ወጥተው ሄዱ፤ ዳዊትም ይህን ስላወቀ በማዖን ምድረ በዳ አለት ወደበዛበት አንድ ኮረብታ አልፎ በዚያ ተቀመጠ፤ ሳኦልም ይህን በሰማ ጊዜ ዳዊትን የመከታተል ተግባሩን ቀጠለ፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ሳኦልና ሰዎቹም ዳዊትን ሊፈልጉት ሄዱ፤ እርሱም ይህን በሰማ ጊዜ፣ ወደ ዐለቱ ወርዶ በማዖን ምድረ በዳ ተቀመጠ። ሳኦልም ይህን እንደ ሰማ፣ ዳዊትን በማሳደድ ወደ ማዖን ምድረ በዳ ዘልቆ ገባ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ሳኦልና ሰዎቹም ዳዊትን ሊፈልጉት ሄዱ፤ እርሱም ይህን በሰማ ጊዜ፥ ወደ ዐለቱ ወርዶ በማዖን ምድረ በዳ ተቀመጠ። ሳኦልም ይህን እንደሰማ፥ ዳዊትን በማሳደድ ወደ ማዖን ምድረ በዳ ዘልቆ ገባ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ሳኦ​ልና ሰዎ​ቹም ሊፈ​ል​ጉት ሄዱ፤ ለዳ​ዊ​ትም ነገ​ሩት፤ እር​ሱም በማ​ዖን ምድረ በዳ ወዳ​ለው ዓለት ወረደ፤ ሳኦ​ልም ያን በሰማ ጊዜ ዳዊ​ትን በማ​ዖን ምድረ በዳ ተከ​ትሎ አሳ​ደ​ደው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ሳኦልና ሰዎቹም ሊፈልጉት ሄዱ፥ ዳዊትም በሰማ ጊዜ ወደ ዓለቱ ወርዶ በማዖን ምድረ በዳ ተቀመጠ፥ ሳኦልም ያንን በሰማ ጊዜ ዳዊትን በማዖን ምድረ በዳ አሳደደው።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 23:25
5 Cross References  

ስለዚህም ሳኦል ዳዊትን የማሳደድ ተግባሩን አቁሞ ፍልስጥኤማውያንን ለመውጋት ሄደ፤ ያም ቦታ “የማምለጥ አለት” ተብሎ የተጠራበት ምክንያት ይኸው ነው።


ወዲያውም ብርቱ አደጋ ጥሎባቸው ከእነርሱ ብዙዎችን ገደለ፤ ከዚህም በኋላ ሄዶ ዔጣም ተብላ በምትጠራ ስፍራ በዋሻ ውስጥ ተቀመጠ።


ስለዚህም እነርሱ ሳኦል ከመሄዱ በፊት ወደ ዚፍ ተመለሱ፤ በዚህን ጊዜ ዳዊትና ተከታዮቹ ከይሁዳ ምድረ በዳ በስተ ደቡብ በኩል በሚገኘው በማዖን በረሓ ነበሩ፤


ሳኦልና ወታደሮቹ ከኮረብታው በአንድ በኩል ሲሆኑ፥ ዳዊትና ተከታዮቹም ከኮረብታው በሌላ በኩል ነበሩ፤ ዳዊትና ተከታዮቹም ሊማርኩአቸው ከተቃረቡት ከሳኦልና ከወታደሮቹ ለማምለጥ በመጣደፍ ላይ ነበሩ።


እግዚአብሔር አለቴ፥ አምባዬ የደኅንነቴ ኀይል፥ ጠንካራ ምሽጌ ነው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements