Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 23:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ከዚህም በኋላ ዳዊት እንዲህ አለ፤ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! በአገልጋይህ በእኔ ሰበብ ሳኦል መጥቶ ቀዒላን ለመደምሰስ ማቀዱን ሰምቻለሁ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ከዚያም ዳዊት እንዲህ አለ፤ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ሳኦል ወደ ቅዒላ መጥቶ፣ በእኔ ምክንያት ከተማዪቱን ለማጥፋት ማሰቡን ባሪያህ በትክክል ሰምቷል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ከዚያም ዳዊት እንዲህ አለ፤ “የእስራኤል አምላክ ጌታ ሆይ፤ ሳኦል ወደ ቅዒላ መጥቶ፥ በእኔ ምክንያት ከተማዪቱን ለማጥፋት ማሰቡን ባርያህ በትክክል ሰምቷል።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ዳዊ​ትም፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ አቤቱ! በእኔ ምክ​ን​ያት ከተ​ማ​ዪ​ቱን ያጠፋ ዘንድ ሳኦል ወደ ቂአላ ሊመጣ እን​ደ​ሚ​ፈ​ልግ እኔ ባሪ​ያህ ፈጽሜ ሰም​ቻ​ለሁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ዳዊትም፦ የእስራኤል አምላክ አቤቱ፥ በእኔ ምክንያት ከተማይቱን ያጠፋ ዘንድ ሳኦል ወደ ቅዒላ ሊመጣ እንደሚፈልግ እኔ ባሪያህ ፈጽሜ ሰምቻለሁ።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 23:10
8 Cross References  

ድኾችን በጭካኔ የሚገዛ መሪ እንደሚያገሣ አንበሳና ተርቦ ምግቡን ለማደን እንደሚያደባ ድብ ነው።


በተለይም መርዶክዮስ አይሁዳዊ መሆኑን በተረዳ ጊዜ መርዶክዮስን ብቻ መግደል በቂ እንዳልሆነ ተገነዘበ፤ ስለዚህም በመላው የፋርስ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ግዛት ውስጥ ያሉትን የመርዶክዮስ ወገን የሆኑትን አይሁድን ሁሉ ለማጥፋት ዕቅድ አወጣ።


ስለዚህም ሳኦል ወታደሮቹን ለጦርነት ጠርቶ ወደ ቀዒላ በመዝመት ዳዊትንና ተከታዮቹን እንዲከቡ አዘዘ።


ከዚህም በኋላ ሳኦል የካህናት ከተማ በሆነችው በኖብ የሚኖሩት ሁሉ ወንዶችና ሴቶች፥ ልጆችና ሕፃናት፥ የቀንድ ከብቶችና አህዮች፥ እንዲሁም የበግ መንጋዎች ሁሉ እንዲገደሉ አደረገ።


በከተማይቱ ውስጥ ኀምሳ ደጋግ ሰዎች ቢገኙ ከተማይቱን በሙሉ ትደመስሳለህን? ስለ ኀምሳው ደጋግ ሰዎች ስትል ከተማይቱ እንዳትጠፋ አታደርግምን?


ዳዊትም ሳኦል አደጋ ሊጥልበት ማቀዱን በሰማ ጊዜ ካህኑን አብያታርን “ኤፉዱን ይዘህ ና!” አለው።


ታዲያ፥ የቀዒላ ከተማ ነዋሪዎች እኔን ለሳኦል አሳልፈው ይሰጡኝ ይሆን? ሳኦልስ እኔ እንደ ሰማሁት ወደዚህ መምጣቱ እውነት ነውን? የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! መልስ እንድትሰጠኝ እለምንሃለሁ!” እግዚአብሔርም “አዎ፥ ሳኦል በእርግጥ ይመጣል” ሲል መለሰለት።


Follow us:

Advertisements


Advertisements