Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 18:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ከዚህም የተነሣ ከዚያን ቀን ጀምሮ በዳዊት ላይ ቅናትና ጥርጣሬ አደረበት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ከዚያች ዕለት አንሥቶ ሳኦል ዳዊትን በቅናት ዐይን ይመለከተው ጀመር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ከዚያች ዕለት አንሥቶ ሳኦል ዳዊትን በቅናት ዐይን ይመለከተው ጀመር።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ከዚ​ያም ቀን ጀምሮ ሳኦል ዳዊ​ትን ሁል​ጊዜ ይጠ​ባ​በ​ቀው ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ከዚያም ቀን ጀምሮ ሳኦል ዳዊትን ተመቅኝቶ ተመለከተው።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 18:9
11 Cross References  

ለዲያብሎስም መግቢያ ቀዳዳ አትስጡት።


አመንዝራነት፥ ስግብግብነት፥ ክፋት፥ አታላይነት፥ ስድነት፥ ምቀኝነት፥ ሐሜተኛነት፥ ትዕቢት፥ ግዴለሽነት ናቸው።


በገዛ ገንዘቤ የፈለግኹትን ማድረግ መብት የለኝምን? ወይስ እኔ ለጋሥ ስለ ሆንኩ አንተ ትመቀኛለህ?’ ”


በላባም ዘንድ እንደ ቀድሞው ተወዳጅ አለመሆኑን ተረዳ።


ወንድሞች ሆይ! በእናንተም ላይ እንዳይፈረድባችሁ እርስ በርሳችሁ አትጨቃጨቁ፤ እነሆ ፈራጁ የሚመጣበት ጊዜ ደርሶአል።


ሳኦል ይህ አባባል ደስ ስላላሰኘው በጣም ተቈጥቶ “ለዳዊት ዐሥር ሺህ፥ ለእኔ ግን አንድ ሺህ ብቻ ሰጡ፤ እንግዲህ ከመንገሥ በቀር ምን ቀረው!” አለ።


በማግስቱም በድንገት ከእግዚአብሔር የተላከ ክፉ መንፈስ ሳኦልን ተቈራኘው፤ በቤቱም ውስጥ እንደ እብድ ይለፈልፍ ነበር፤ ዳዊትም በየቀኑ ያደርግ በነበረው ዐይነት ለሳኦል በገና ይደረድርለት ነበር፤ ሳኦልም ጦሩን በእጁ ይዞ ነበር።


ሳኦል ዳዊትን ሊገድለው ማቀዱን ለልጁ ለዮናታንና ባለሟሎቹ ለሆኑት ባለሥልጣኖች ሁሉ ነገረ፤ ነገር ግን ዮናታን ዳዊትን እጅግ ይወደው ነበር።


ቊጣ ጭካኔና ንዴትን ያስከትላል፤ ቅናት ግን ከቊጣ የባሰ ነው።


ደግሞም ሰዎች የተመኙትን ለማግኘት ተግተው በመሥራት ምን ያኽል እንደሚደክሙ ተመለከትኩ፤ ይህንንም የሚያደርጉት በባልንጀሮቻቸው ላይ በመቅናት መሆኑን ተረዳሁ፤ ይህም ሁሉ ከንቱ ስለ ሆነ ነፋስን ለመጨበጥ እንደ መሞከር ነው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements