Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 18:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ከዚህም የተነሣ ሳኦል ዳዊትን ከፊቱ ለማራቅ የሺህ ወታደሮች አዛዥ አድርጎ ላከው፤ ዳዊትም ወታደሮቹን ወደ ጦርነት መራ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ስለዚህ ዳዊትን ከአጠገቡ በማራቅ የሺሕ አለቃ አደረገው። ዳዊትም ሰራዊቱን እየመራ በፊታቸው ይወጣና ይገባ ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ስለዚህ ዳዊትን ከአጠገቡ በማራቅ የሺህ አለቃ አደረገው። ዳዊትም ሠራዊቱን እየመራ በፊታቸው ይወጣና ይገባ ነበር።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ስለ​ዚ​ህም ሳኦል ከእ​ርሱ አራ​ቀው፤ የሺህ አለ​ቃም አድ​ርጎ ሾመው፤ በሕ​ዝ​ቡም ፊት ይወ​ጣና ይገባ ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ስለዚህም ሳኦል ከእርሱ አራቀው፥ የሺህ አለቃም አደረገው፥ በሕዝቡም ፊት ይወጣና ይገባ ነበር።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 18:13
7 Cross References  

ከአሁን በፊት ሳኦል የእኛ ንጉሥ በነበረ ጊዜ እንኳ በጦርነት እስራኤልን የምትመራ አንተ ነበርክ፤ እንዲሁም ሕዝቡን እስራኤልን እንድትመራና በእስራኤልም ላይ እንድትነግሥ እግዚአብሔር ቃል ገብቶልሃል።”


ከቤትህ ወጥተህ ስትሄድና ወደ ቤትህም ስትመለስ ዛሬም ለዘለዓለሙ ይጠብቅሃል።


ሳኦልም ባለሟሎችን እንዲህ አላቸው፤ “እናንተ የብንያም ሰዎች አድምጡኝ! በውኑ የእሴይ ልጅ ዳዊት ለሁላችሁም ለእያንዳንዳችሁ የእርሻ መሬትና የወይን ተክል ቦታ የሚሰጣችሁና በሠራዊቱም ውስጥ ሻለቆችና የመቶ አለቆች አድርጎ የሚሾማችሁ ይመስላችኋልን?


ሳኦልም እንደ ገና “ንጉሡ ስለ ልጁ ከአንተ የሚፈልገው ጥሎሽ ጠላቶቹን መበቀል እንዲችል አንድ መቶ ፍልስጥኤማውያን ገድለህ ሸለፈታቸውን እንድታመጣለት ብቻ ነው” ብላችሁ ንገሩት ሲል ባለሟሎቹን አዘዘ። ሳኦል ይህን ያደረገበት ምክንያት ዳዊት በፍልስጥኤማውያን እጅ እንዲገደልለት በማቀድ ነበር።


ከእነርሱም አንዳንዶቹን የሺህ አለቆችና የኀምሳ አለቆች አድርጎ ይሾማል፤ ወንዶቹ ልጆቻችሁ የንጉሡ ሁዳድ አራሾችና መከር ሰብሳቢዎች ይሆናሉ፤ ሌሎችም የጦር መሣሪያና የሠረገላ ዕቃ ሠራተኞች ይሆናሉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements