Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 17:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ሦስቱ ታላላቅ ልጆቹም ከሳኦል ጋር ወደ ጦርነት ዘምተው ነበር፤ እነርሱም በኲሩ ኤሊአብ፥ ሁለተኛው አሚናዳብ፥ ሦስተኛውም ሻማ ተብለው ይጠሩ ነበር።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ሦስቱ የእሴይ ታላላቅ ልጆች ሳኦልን ተከትለው ወደ ጦርነት ሄደው ነበር፤ እነርሱም ታላቁ ኤልያብ፣ ሁለተኛው አሚናዳብ፣ ሦስተኛውም ሣማ ይባላሉ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ሦስቱ የእሴይ ታላላቅ ልጆች ሳኦልን ተከትለው ወደ ጦርነት ሄደው ነበር፤ እነርሱም ታላቁ ኤሊአብ፥ ሁለተኛው አሚናዳብ፥ ሦስተኛውም ሻማ ይባላሉ፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 የእ​ሴ​ይም ሦስቱ ታላ​ላ​ቆች ልጆቹ ሳኦ​ልን ተከ​ት​ለው ወደ ሰልፉ ሄደው ነበር፤ ወደ ሰል​ፉም የሄ​ዱት የሦ​ስቱ ልጆች ስም ይህ ነበረ፤ ታላቁ ኤል​ያብ፥ ሁለ​ተ​ኛ​ውም አሚ​ና​ዳብ፥ ሦስ​ተ​ኛ​ውም ሣማዕ ነበረ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 የእሴይም ሦስቱ ታላላቆች ልጆቹ ሳኦልን ተከትለው ወደ ሰልፉ ሄደው ነበር፥ ወደ ሰልፉም የሄዱት የሦስቱ ልጆቹ ስም ይህ ነበረ፥ ታላቁ ኤልያብ ሁለተኛውም አሚናዳብ ሦስተኛውም ሣማ ነበረ።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 17:13
6 Cross References  

እሴይ የበኲር ልጁን ኤሊአብንና ሁለተኛውን አሚናዳብን፥ ሦስተኛውን ሻማን፥


እርሱም እስራኤላውያንን በብርቱ ተፈታተነ፤ ይሁን እንጂ እርሱን የዳዊት ወንድም የሻማ ልጅ ዮናታን ገደለው።


የዳዊት ወንድም የሻማ ልጅ ዮናዳብ ግን እንዲህ አለ፤ “ጌታዬ ሆይ! የተገደሉት ልዑላኑ በሙሉ አይደሉም፤ የተገደለው አምኖን ብቻ ነው፤ አቤሴሎም ይህን ለማድረግ ያቀደው አምኖን የእኅቱን የትዕማርን ክብረ ንጽሕና ከደፈረበት ጊዜ አንሥቶ እንደ ነበር ፊቱን አይተህ መረዳት ትችላለህ።


ነገር ግን በጣም ዘዴኛ የሆነ፥ ዮናዳብ ተብሎ የሚጠራ ወዳጅ ነበረው፤ እርሱም የዳዊት ወንድም የሻማ ልጅ ነበር፤


የዳዊት ታላቅ ወንድም ኤሊአብም ዳዊት ከሰዎቹ ጋር ሲነጋገር ሰማ፤ እርሱም በዳዊት ላይ በጣም ተቈጥቶ “እዚህ ምን ትሠራለህ? በበረሓ ያሉትንስ እነዚያን ጥቂቶች በጎችህን ለማን ተውካቸው? እኔ ትዕቢተኛነትህንና የልብህን ክፋት ዐውቃለሁ! አሁን የመጣኸው እኮ የጦርነቱን ሁኔታ ለመመልከት ነው!” አለው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements