Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 17:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ፍልስጥኤማውያን ሶኮ ተብላ በምትጠራው በይሁዳ ለጦርነት ተሰለፉ፤ እነርሱም በሶኮና በዐዜቃ መካከል ኤፌስዳሚም ተብሎ በሚጠራው ቦታ ሰፍረው ነበር።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ፍልስጥኤማውያን ሰራዊታቸውን ለጦርነት አሰባስበው፣ በይሁዳ ምድር በሦኮን ላይ አከማቹ፤ እነርሱም በሰኰትና በዓዜቃ መካከል ባለው በኤፌሰደሚም ሰፈሩ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ፍልስጥኤማውያን ሠራዊታቸውን ለጦርነት አሰባስበው፥ በይሁዳ ምድር በሰኮ ላይ አከማቹ፤ በሰኮና በዓዜቃ መካከል ባለው በኤፌስደሚምም ሰፈሩ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ጭፍ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ለጦ​ር​ነት ሰበ​ሰቡ፤ ራሳ​ቸ​ውም በይ​ሁዳ በሰ​ኮት ተሰ​በ​ሰቡ፤ በሰ​ኮ​ትና በዓ​ዜቃ መካ​ከል በኤ​ፌ​ር​ሜም ሰፈሩ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ፍልስጥኤማውያንም ጭፍሮቻቸውን በይሁዳ ባለው በሰኮት አከማቹ፥ በሰኮትና በዓዜቃ መካከል በአርፌስደሚም ሰፈሩ።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 17:1
11 Cross References  

ያርሙት፥ ዐዱላም፥ ሶኮህ፥ ዐዜቃ፥


በዚሁ ጊዜ ፍልስጥኤማውያን በምዕራባዊ ኰረብቶች ግርጌና በደቡባዊ ይሁዳ የሚገኙትን ታናናሽ ከተሞች ወረሩ፤ ቤትሼሜሽ፥ አያሎን፥ ገዴሮት፥ ሶኮ፥ ቲምናና ጊምዞ ተብለው የሚጠሩትን ከተሞችና በዙሪያቸው የሚገኙትን መንደሮች በድል አድራጊነት ያዙ፤ በዚያም ኖሩ።


እርሱ ፍልስጥኤማውያን ለጦርነት በተሰለፉ ጊዜ በፓስደሚም ከዳዊት ጋር ነበር፤ የገብስ ማሳ በነበረበት ቦታ እስራኤላውያን ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ።


ፍልስጥኤማውያንም እስራኤላውያንን ለመውጋት ተሰበሰቡ፤ እነርሱም ከሠላሳ ሺህ የጦር ሠረገሎችና ከስድስት ሺህ ፈረሰኞች ጋር ብዛቱ እንደ ባሕር ዳር አሸዋ የበዛ ሠራዊት ነበራቸው፤ ሄደውም በቤትአዌን በስተምሥራቅ ሚክማስ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ መሸጉ።


በምድሪቱ ላይ የቀሩትም፥ አምስቱ የፍልስጥኤማውያን መሪዎች፥ ከነዓናውያን በሙሉ፥ ሲዶናውያንና ከባዓልሔርሞን ተራራ አንሥቶ እስከ ሐማት ድረስ በሊባኖስ ተራራዎች የሚኖሩት ሒዋውያን ነበሩ።


የባቢሎን ንጉሥ ሠራዊት በኢየሩሳሌም ከዚያም አልፎ ላኪሽና ዐዜቃ ተብለው በሚጠሩት፥ በይሁዳ ቀርተው በነበሩት የመጨረሻ የተመሸጉ ከተሞች ላይ አደጋ እየጣለ ነበር።


ቤትጹር፥ ሶኮ፥ ዐዱላም፥


ሳኦል በነበረበት ዘመን ሁሉ ከፍልስጥኤማውያን ጋር በብርቱ ጠላትነት ሲዋጋ ኖረ፤ ስለዚህም ብርቱ ወይም ጀግና የሆነ ሰው ሲያገኝ እየመለመለ በጦር ሠራዊቱ ውስጥ ያስመዘግበው ነበር።


ከዚያም በኋላ ሳኦል ፍልስጥኤማውያንን ከማሳደድ ተገታ፤ እነርሱም ተመልሰው ወደ አገራቸው ሄዱ።


እስራኤላውያን በምጽጳ መሰብሰባቸውንም ፍልስጥኤማውያን በሰሙ ጊዜ አምስቱ የፍልስጥኤም ገዢዎች አደጋ ሊጥሉባቸው ወጡ፤ እስራኤላውያንም ይህን በሰሙ ጊዜ ፈሩ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements