Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 16:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ሳሙኤልም “ይህን ለማድረግ እንዴት ይቻለኛል? ሳኦል ይህን ቢሰማ ይገድለኛል!” ሲል ጠየቀ። እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “ ‘ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ለማቅረብ መጥቻለሁ’ ብለህ ጊደር ይዘህ ሂድ፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ሳሙኤል ግን፣ “ሳኦል ከሰማ ስለሚገድለኝ እንዴት መሄድ እችላለሁ?” አለ። እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ “አንዲት ጊደር ይዘህ ሂድና፣ ‘ለእግዚአብሔር ልሠዋ መጥቻለሁ’ በል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ሳሙኤል ግን፥ “ሳኦል ከሰማ ስለሚገድለኝ እንዴት መሄድ እችላለሁ?” አለ። ጌታም እንዲህ አለው፤ “አንዲት ጊደር ይዘህ ሂድና፥ ‘ለጌታ ልሠዋ መጥቻለሁ’ በል።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ሳሙ​ኤ​ልም፥ “እን​ዴት እሄ​ዳ​ለሁ? ሳኦል ቢሰማ ይገ​ድ​ለ​ኛል” አለ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “አን​ዲት ጊደር ይዘህ ሂድና፦ ‘ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እሠዋ ዘንድ መጣሁ’ በል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ሳሙኤልም፦ እንዴት እሄዳለሁ? ሳኦል ቢሰማ ይገድለኛል አለ። እግዚአብሔርም፦ አንዲት ጊደር ይዘህ ሂድና፦ ለእግዚአብሔር እሠዋ ዘንድ መጣሁ በል።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 16:2
8 Cross References  

ልጃገረዶቹም “አዎን! እነሆ፥ ሕዝቡ ዛሬ በኮረብታው ላይ መሥዋዕትን ስለሚያቀርብ ባለራእዩ ወደ ከተማይቱ መጥቶአልና ፈጥናችሁ ድረሱበት፤


‘የእኛ ቤተሰብ በከተማው ውስጥ መሥዋዕት ስለሚያቀርብና ወንድሜም በዚያ እንድገኝ ስላዘዘኝ በአንተ ዘንድ ሞገስን አግኝቼ ከሆነ እባክህ ፍቀድልኝና ወንድሞቼን ለማየት ልሂድ’ ብሎ ጠይቆኝ ነበር፤ በዚህ ምክንያት በንጉሡ ግብር ላይ አልተገኘም።”


“እነሆ! እንደ በጎች በተኲላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ብልኆች፥ እንደ ርግብ የዋሆች ሁኑ።


ማርያም መልአኩን “እኔ ድንግል ነኝ፤ ታዲያ፥ ይህ ነገር እንዴት ሊሆን ይችላል?” አለችው።


ሙሴ ግን እግዚአብሔርን “ወደ ፈርዖን ሄጄ የእስራኤልን ልጆች ከግብጽ ለማውጣት እኔ ማን ነኝ?” አለ።


እሴይንም ወደ መሥዋዕቱ እንዲመጣ ጥራው፤ እኔም የምታደርገውን ነገር እነግርሃለሁ፤ እኔ የምነግርህንም ሰው ቀብተህ ታነግሣለህ።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements