Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 14:47 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

47 ሳኦል በእስራኤል ከነገሠ በኋላ፥ በሁሉም ስፍራ የሚገኙ ጠላቶቹን ወጋ፤ እነርሱም የሞአብ፥ የዐሞንና የኤዶም ሕዝቦች፥ የጾባ ነገሥታትና ፍልስጥኤማውያን ናቸው፤ በተዋጋበት ስፍራ ሁሉ ድል አድራጊ ሆነ፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

47 ሳኦል በእስራኤል ላይ በትረ መንግሥቱን ከጨበጠ በኋላ፣ በዙሪያው ያሉትን ጠላቶቹን ማለትም ሞዓብን፣ አሞናውያንን፣ ኤዶምን፣ የሱባን ነገሥታትና ፍልስጥኤማውያንን ወጋቸው። በሄደበት ሁሉ ድል ይነሣ ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

47 ሳኦል በእስራኤል ላይ ከነገሠ በኋላ፥ በዙሪያው ያሉትን ጠላቶቹን ሞዓብን፥ አሞናውያንን፥ ኤዶምን፥ የጾባን ነገሥታትና ፍልስጥኤማውያንን ወጋቸው። በተዋጋበት ስፍራ ሁሉ ድል አድራጊ ነበር።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

47 ሳኦ​ልም መን​ግ​ሥ​ቱን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አጸና፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ካሉት ከጠ​ላ​ቶቹ ሁሉ ጋር፥ ከሞ​ዓ​ብም፥ ከአ​ሞ​ንም ልጆች፥ ከኤ​ዶ​ም​ያ​ስም፥ ከቢ​ዖ​ርም፥ ከሱ​ባም ነገ​ሥ​ታት፥ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ሁሉ ጋር ይዋጋ ነበር፤ በየ​ሄ​ደ​በ​ትም ሁሉ ድል ይነሣ ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

47 ሳኦልም መንግሥቱን በእስራኤል ላይ አጸና፥ በዙሪያውም ካሉት ከጠላቶቹ ሁሉ ጋር፥ ከሞዓብም፥ ከአሞንም ልጆች፥ ከኤዶምያስም፥ ከሱባም ነገሥታት፥ ከፍልስጥኤማውያንም ጋር ይዋጋ ነበር፥ በየሄደበትም ሁሉ ድል ይነሣ ነበር።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 14:47
17 Cross References  

ዐሞናውያን ዳዊትን በገዛ እጃቸው ጠላት እንዳደረጉት ተገነዘቡ፤ ስለዚህም እግረኛ ወታደሮችን ከቤትረሖብና ከጾባ ኻያ ሺህ ሶርያውያንንና ከጦብ ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰዎችን፤ እንዲሁም ከንጉሥ ማዕካ አንድ ሺህ ሰዎችን ቀጠሩ፤


ሳኦል በነበረበት ዘመን ሁሉ ከፍልስጥኤማውያን ጋር በብርቱ ጠላትነት ሲዋጋ ኖረ፤ ስለዚህም ብርቱ ወይም ጀግና የሆነ ሰው ሲያገኝ እየመለመለ በጦር ሠራዊቱ ውስጥ ያስመዘግበው ነበር።


ይሁን እንጂ እነርሱ ለዘለዓለም ፈጽሞ እንዲደመሰሱ ደግሞ የእግዚአብሔር ፈቃድ አልነበረም፤ ስለዚህም በዳግማዊ ኢዮርብዓም አማካይነት አዳናቸው።


እንደገናም እግዚአብሔር ረዞን ተብሎ የሚጠራውን የኤሊዓዳን ልጅ በሰሎሞን ላይ ጠላት አድርጎ አስነሣ፤ ረዞን የጾባ ንጉሥ ከነበረው ከጌታው ከሀዳድዔዜር ኮብልሎ፥


ከዚያም በኋላ ዳዊት የሶርያ ግዛት የሆነችው የጾባ ንጉሥ የሆነውን የረሖብን ልጅ ሀዳድዔዜርን ድል አደረገ፤ ሀዳድዔዜር ድል በተመታበትም ጊዜ በላይኛው ኤፍራጥስ ወንዝ የሚገኘውን ግዛቱን ለማስመለስ በጒዞ ላይ ነበር።


ሳኦል ሲነግሥ ዕድሜው 30 ዓመት ነበር፤ በእስራኤልም ላይ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት


ከእንግዲህ ወዲህ የሚመራችሁ ንጉሥ አግኝቼአለሁ፤ እኔ ግን ዕድሜዬ ስለ ገፋ ሸምግዬአለሁ፤ ልጆቼም ከእናንተው ጋር አሉ፤ ከወጣትነት ጊዜዬ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ የእናንተ መሪ ሆኜ ቈይቼአለሁ።


ከዚያም በኋላ ሳኦል ፍልስጥኤማውያንን ከማሳደድ ተገታ፤ እነርሱም ተመልሰው ወደ አገራቸው ሄዱ።


የሳኦል እረኞች አለቃ የሆነው ኤዶማዊው ዶይቅ በዚያኑ ቀን ሃይማኖታዊ ሥርዓትን ለመፈጸም በዚያ ተገኝቶ ነበር።


ታላቂቱ ወንድ ልጅ ወለደችና ስሙን ሞአብ አለችው፤ እርሱ ዛሬ ሞአባውያን ተብለው ለሚጠሩት ሕዝቦች ቅድመ አያት ነው።


ታናሽቱም ወንድ ልጅ ወለደችና ስሙን ቤንዐሚ አለችው፤ እርሱ ዛሬ ዐሞናውያን ተብለው ለሚጠሩት ሕዝቦች ቅድመ አያት ነው።


ኤዶም የተባለው የዔሳው የትውልድ ታሪክ የሚከተለው ነው፤


ስለዚህ ኤዶም የተባለው ዔሳው በተራራማው አገር በኤዶም ተቀመጠ።


እነዚህ ሁሉ ኤዶም የተባለው የዔሳው ልጆችና የነገድ አለቆች ናቸው።


የዮናታን ቀስት ሳይገድል የማይመለስ፥ የሳኦልም ሰይፍ ጠላትን የሚቈራርጥ ኀያላንን መትቶ የሚሰብር፥ ጠላትን የሚገድል ነበር።


በዚህ ዐይነት ዳዊት የመላው እስራኤል ንጉሥ ሆኖ ሕዝቡ ዘወትር ትክክለኛ ፍርድ ማግኘት እንዲችል ጥረት ያደርግ ነበር፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements