1 ሳሙኤል 14:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም21 ከፍልስጥኤማውያን ጋር በመተባበር ወደ ጦሩ ሰፈር ሄደው የነበሩ አንዳንድ ዕብራውያንም ፍልስጥኤማውያንን ከድተው ከሳኦልና ከዮናታን ጋር ተባበሩ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም21 እነዚያ ቀድሞ ከፍልስጥኤማውያን ጐን ተሰልፈው የነበሩትና ዐብረዋቸውም ወደ ሰፈራቸው የወጡት ዕብራውያን ከሳኦልና ከዮናታን ጋራ ወደ ነበሩት እስራኤላውያን ገቡ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)21 እነዚያ ቀድሞ ከፍልስጥኤማውያን ጐን ተሰልፈው የነበሩትና አብረዋቸውም ወደ ሰፈራቸው የወጡት ዕብራውያን ከሳኦልና ከዮናታን ጋር ወደነበሩት እስራኤላውያን ገቡ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)21 ቀድሞ ከፍልስጥኤማውያን ጋር የነበሩና ወደ ሠራዊቱ የወጡ አገልጋዮችም ከሳኦልና ከዮናታን ጋር ወደ ነበሩ እስራኤላውያን ለመሆን ተመለሱ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)21 ቀድሞ ከፍልስጥኤማውያን ጋር የነበሩት ከእነርሱም ጋር ከሰፈሩ ዙሪያ የወጡት ዕብራውያን ደግሞ ከሳኦልና ከዮናታን ጋር ወደ ነበሩት እስራኤላውያን ለመሆን ዞሩ። See the chapter |