Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 14:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እነርሱም ወጣ ብለው ለፍልስጥኤማውያን ታዩአቸው፤ ፍልስጥኤማውያንም “እነሆ! አንዳንድ ዕብራውያን ከተሸሸጉበት ጒድጓድ በመውጣት ላይ ናቸው!” ተባባሉ፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ሁለቱም ለፍልስጥኤማውያን ጭፍራ በታዩ ጊዜ፣ ፍልስጥኤማውያን፣ “እነሆ፤ ዕብራውያን ከተደበቁባቸው ጕድጓዶች እየወጡ ነው” አሉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ሁለቱም ለፍልስጥኤማውያን ሠራዊት በታዩ ጊዜ፥ ፍልስጥኤማውያን፥ “እነሆ፤ ዕብራውያን ከተደበቁባቸው ጉድጓዶች እየወጡ ነው” አሉ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ሁለ​ታ​ቸ​ውም ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሰፈር ገቡ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም “እነሆ፥ ዕብ​ራ​ው​ያን ከተ​ሸ​ሸ​ጉ​በት ጕድ​ጓድ ይወ​ጣሉ” አሉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ሁለታቸውም ለፍልስጥኤማውያን ጭፍራ ተገለጡ፥ ፍልስጥኤማውያንም፦ እነሆ፥ ዕብራውያን ከተሸሸጉበት ጉድጓድ ይወጣሉ አሉ።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 14:11
5 Cross References  

እስራኤላውያን ሁኔታው አስጊ መሆኑን ባዩና ሠራዊቱም መዋከቡን በተመለከቱ ጊዜ በዋሻ፥ በሾኽ ቊጥቋጦ፥ በአለቶች መካከል በጒድጓዶችና በጒድባ ውስጥ ተሸሸጉ፤


በኤፍሬም ኮረብታዎች ተደብቀው የነበሩ ሌሎች እስራኤላውያንም ፍልስጥኤማውያን በሽሽት ላይ መሆናቸውን ሰሙ፤ ስለዚህም ከወገን ጦር ጋር ተባብረው ፍልስጥኤማውያንን ማሳደድ ጀመሩ፤


የምድያማውያን ኀይል በእስራኤል ላይ በረታ፤ በእነርሱም ምክንያት የእስራኤል ሕዝብ መሸሸጊያ ቦታ፥ ዋሻና ምሽግ አዘጋጁ።


በፍርሃት ይጨነቃሉ፤ በመንቀጥቀጥም ከምሽጋቸው ወጥተው ወደ እኔ ይመጣሉ።


የፍልስጥኤም ጦር አዛዦችም እነርሱን ባዩ ጊዜ “እነዚህ ዕብራውያን እዚህ ምን ይሠራሉ?” ሲሉ ጠየቁ። አኪሽም “ይህማ የእስራኤል ንጉሥ ባለሟል የነበረው ዳዊት አይደለምን? እነሆ እርሱ ከእኔ ጋር ሲኖር ብዙ ጊዜው ነው፤ ሳኦልን ከድቶ ወደ እኔ ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ ሊያሳዝነኝ የሚችል ምንም ዐይነት በደል ሠርቶ አልተገኘም” ሲል መለሰ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements