Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 13:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ፍልስጥኤማውያን የሚክማስን መተላለፊያ የሚቈጣጠር አንድ ቡድን ላኩ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 በዚያ ጊዜ አንድ የፍልስጥኤማውያን ጭፍራ ወደ ማክማስ መተላለፊያ ወጥቶ ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 በዚያን ጊዜ አንድ የፍልስጥኤማውያን የጦር ምድብ የሚክማስን መተላለፊያ ለመቆጣጠር ወጣ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ከዚ​ያም ጥቂ​ቶች ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሰፈር ወደ ማኪ​ማስ መተ​ላ​ለ​ፊያ ወጡ።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 13:23
7 Cross References  

የጠላት ሠራዊት ወደ ዓይ ከተማ ደረሰ፤ በሚግሮንም በኩል ሲያልፉ ጓዛቸውን በሚክማስ አኖሩ።


አንድ ቀን የሳኦል ልጅ ዮናታን የጦር መሣሪያ የሚሸከምለትን ወጣት ጋሻ ጃግሬውን “ወደ ፍልስጥኤማውያን የጦር ሰፈር እንሻገር” አለው። ነገር ግን ዮናታን ይህን ጉዳይ ለአባቱ እንኳ አልነገረውም፤


ዳዊት በዚያን ጊዜ በተመሸገ ኮረብታ ላይ ነበር፤ ከፍልስጥኤማውያን ሠራዊት አንድ ቡድን ቤተልሔምን በመውረር ያዘ፤


ፍልስጥኤማውያንም እስራኤላውያንን ለመውጋት ተሰበሰቡ፤ እነርሱም ከሠላሳ ሺህ የጦር ሠረገሎችና ከስድስት ሺህ ፈረሰኞች ጋር ብዛቱ እንደ ባሕር ዳር አሸዋ የበዛ ሠራዊት ነበራቸው፤ ሄደውም በቤትአዌን በስተምሥራቅ ሚክማስ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ መሸጉ።


መተላለፊያውን አልፈው ዐዳር በጌባዕ ሆነ በራማ ከተማ የሚኖሩ ሁሉ ደነገጡ፤ በንጉሥ ሳኦል ከተማ በጊብዓ የሚኖሩትም ሁሉ ሸሹ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements