1 ሳሙኤል 11:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 ከያቤሽ የመጡትንም መልእክተኞች “ነገ ከቀትር በፊት የምናድናቸው መሆኑን ለሕዝባችሁ ንገሩ” አሉአቸው። መልእክቱንም ለያቤሽ ሰዎች በነገሩ ጊዜ የያቤሽ ሰዎች እጅግ ተደሰቱ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 ከዚያ ለመጡትም መልእክተኞች፣ “ለኢያቢስ ገለዓድ ሰዎች፣ ‘ነገ ፀሓይ ሞቅ በሚልበት ጊዜ ነጻ ትሆናላችሁ’ ብላችሁ ንገሯቸው” አሏቸው። መልእክተኞቹም ሄደው ለኢያቢስ ሰዎች ይህንኑ በነገሯቸው ጊዜ በደስታ ፈነደቁ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 ከዚያ ለመጡትም መልእክተኞች፥ “ለያቢሽ ገለዓድ ሰዎች፥ ‘ነገ ፀሓይ ሞቅ በሚልበት ጊዜ ነጻ ትሆናላችሁ’ ብላችሁ ንገሯቸው” አሏቸው። መልእክተኞቹም ሄደው ለያቢሽ ሰዎች ይህንኑ በነገሯቸው ጊዜ እጅግ ተደሰቱ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 የመጡትንም መልእክተኞች፥ “የኢያቢስ ገለዓድን ሰዎች፦ ነገ ፀሐይ በተኰሰ ጊዜ ድኅነት ይሆንላችኋል በሉአቸው” አሉአቸው። መልእክተኞችም ወደ ከተማዪቱ መጥተው ለኢያቢስ ሰዎች ነገሩ፤ ደስም አላቸው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 የመጡትንም መልክተኞች፦ የኢያቢስ ገለዓድን ሰዎች፦ ነገ ፀሐይ በተኮሰ ጊዜ ማዳን ይሆንላችኋል በሉአቸው አሉአቸው። መልክተኞችም መጥተው ለኢያቢስ ሰዎች ነገሩ፥ ደስም አላቸው። See the chapter |