ሶፎንያስ 3:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 እነሆ በዚያ ዘመን፥ ያስጨነቁሽን ሁሉ እቀጣለሁ፤ አንካሳይቱንም አድናለሁ፥ የተጣለችውንም እሰበስባታለሁ፤ ባፈሩባትም ምድር ሁሉ ላይ ለምስጋናና ለከበረ ስም አደርጋቸዋለሁ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም19 በዚያ ጊዜ፣ ያስጨነቁሽን ሁሉ እቀጣለሁ፤ ዐንካሶችን እታደጋለሁ፤ የተበተኑትንም እሰበስባለሁ፤ በተዋረዱበት ምድር ሁሉ፣ ለውዳሴና ለክብር አደርጋቸዋለሁ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 የሚያስጨንቁሽን ሁሉ በዚያን ጊዜ እቀጣለሁ፤ ያነከሱትን ሁሉ አድናለሁ፤ የተገለሉትን መልሼ እሰበስባቸዋለሁ፤ ኀፍረት እንዲሰማቸው ተደርገው በነበሩበት ቦታ ሁሉ ኀፍረታቸውን ወደ ምስጋናና ክብር እለውጣለሁ።” See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 በዚያ ዘመን እነሆ፥ ባስጨነቁሽ ሁሉ ላይ አደርግባቸዋለሁ፣ አንካሳይቱንም አድናለሁ፥ የተጣለችውንም እሰበስባታለሁ፣ ባፈሩባትም ምድር ሁሉ ላይ ለምስጋናና ለከበረ ስም አደርጋቸዋለሁ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 በዚያ ዘመን እነሆ፥ ባስጨነቁሽ ሁሉ ላይ አደርግባቸዋለሁ፥ አንካሳይቱንም አድናለሁ፥ የተጣለችውንም እሰበስባታለሁ፥ ባፈሩባትም ምድር ሁሉ ላይ ለምስጋናና ለከበረ ስም አደርጋቸዋለሁ። See the chapter |