ዘካርያስ 9:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 ደሙንም ከአፉ ውስጥ፥ ርኩሱንም ነገር ከጥርሱ መካከል አስወግዳለሁ፤ እርሱም ደግሞ ለአምላካችን ቀሪ ሕዝብ ይሆናል፥ በይሁዳም እንደ አለቃ ይሆናል፥ አቃሮንም እንደ ኢያቡሳዊ ይሆናል። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም7 ደሙን ከአፋቸው፣ አስጸያፊውንም ምግብ ከመንጋጋቸው አወጣለሁ። የተረፉት ለአምላካችን ይሆናሉ፤ በይሁዳም አለቆች ይሆናሉ፤ አቃሮንም እንደ ኢያቡሳዊ ይሆናል። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 ከእንግዲህ ወዲህ ደም ያለበትን ጥሬ ሥጋ ወይም ማንኛውንም የተከለከለ ምግብ አይበሉም፤ ከእነርሱ የተረፉት ከሕዝቤ ተቀላቅለው ከይሁዳ ነገድ እንደ አንድ ጐሣ ይሆናሉ፤ የዔቅሮን ሕዝብ ልክ እንደ ኢያቡሳውያን ከሕዝቡ ጋር ይቀላቀላሉ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 ደሙንም ከአፉ ውስጥ ርኩሱንም ነገር ከጥርሱ መካከል አስወግዳለሁ፣ እርሱም ደግሞ ለአምላካችን ቅሬታ ይሆናል፣ በይሁዳም እንደ አለቃ ይሆናል፥ አቃሮንም እንደ ኢያቡሳዊ ይሆናል። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 ደሙንም ከአፉ ውስጥ ርኩሱንም ነገር ከጥርሱ መካከል አስወግዳለሁ፥ እርሱም ደግሞ ለአምላካችን ቅሬታ ይሆናል፥ በይሁዳም እንደ አለቃ ይሆናል፥ አቃሮንም እንደ ኢያቡሳዊ ይሆናል። See the chapter |