ዘካርያስ 9:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 የጌታ ቃል ትንቢት በሴድራክ ምድር ላይ ይወርዳል፥ በደማስቆም ላይ ያርፋል፤ የእስራኤል ነገድ እንደ ሆነው ሁሉ፥ የአራም ከተሞች የጌታ ናቸው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም1 የእግዚአብሔር ቃል ንግር በሴድራክ ምድር ላይ ይወርድበታል፤ በደማስቆም ላይ ያርፍበታል፤ የሰዎችና የእስራኤል ነገዶች ሁሉ ዐይን፣ በእግዚአብሔር ላይ ዐርፏልና። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 የሰዎችና የእስራኤል ነገዶች ዐይኖች ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ይመለከታሉ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር በሐድራክና በደማስቆ ከተሞች ላይ ይፈርዳል። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 የእግዚአብሔር ቃል ሸክም በሴድራክ ምድር ላይ ነው፥ በደማስቆም ላይ ያርፋል፣ የእግዚአብሔር ዓይን ወደ ሰውና ወደ እስራኤል ነገድ ሁሉ ዘንድ ነው፣ See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 የእግዚአብሔር ቃል ሸክም በሴድራክ ምድር ላይ ነው፥ በደማስቆም ላይ ያርፋል፥ የእግዚአብሔር ዓይን ወደ ሰውና ወደ እስራኤል ነገድ ሁሉ ዘንድ ነው፥ See the chapter |