ዘካርያስ 4:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 እርሱም፦ “የምታየው ምንድነው?” አለኝ። እኔም፦ “እነሆ፥ ሁለንተናው ወርቅ የሆነ መቅረዝ ይታየኛል፤ የዘይት ማሰሮም በላዩ ላይ ነበረ። በመቅረዙም ላይ ሰባት ቧንቧዎች ያሏቸው ሰባት መብራቶች ነበሩ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም2 እርሱም፣ “ምን ታያለህ?” አለኝ። እኔም እንዲህ አልሁ፤ “እነሆ፤ በዐናቱ ላይ የዘይት ማሰሮ ያለበት ሁለንተናው ወርቅ የሆነ መቅረዝ አየሁ፤ በመቅረዙም ላይ ሰባት ቧንቧዎች ያሏቸው ሰባት መብራቶች ነበሩ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 “ይህ የምታየው ምንድን ነው?” ብሎም ጠየቀኝ። እኔም እንዲህ ብዬ መለስኩለት፦ “ሰባት መብራቶች ያሉበት አንድ የወርቅ መቅረዝ አያለሁ፤ በአናቱም ላይ የዘይት ማሰሮ አለ፤ ሰባቱም መብራቶች የክር ማስተላለፊያ ቧንቧ አላቸው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 እርሱም፦ የምታየው ምንድር ነው? አለኝ። እኔም፦እነሆ፥ ሁለንተናው ወርቅ የሆነውን መቅረዝ አየሁ፣ የዘይትም ማሰሮ በራሱ ላይ ነበረ፥ ሰባትም መብራቶች ነበሩበት፣ በራሱም ላይ ለነበሩት መብራቶች ሰባት ቧንቧዎች ነበሩአቸው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 እርሱም፦ የምታየው ምንድር ነው? አለኝ። እኔም፦ እነሆ፥ ሁለንተናው ወርቅ የሆነውን መቅረዝ አየሁ፥ የዘይትም ማሰሮ በራሱ ላይ ነበረ፥ ሰባትም መብራቶች ነበሩበት፥ በራሱም ላይ ለነበሩት መብራቶች ሰባት ቧንቧዎች ነበሩአቸው። See the chapter |