ዘካርያስ 3:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 “የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ በመንገዴ ብትሄድ ትእዛዜንም ብትጠብቅ፥ በቤቴ ላይ ትፈርዳለህ፥ አደባባዮቼንም ትጠብቃለህ፤ እኔም በዚህ ስፍራ ከቆሙት ጋር ስፍራን እሰጥሃለሁ።” See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም7 “የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘በመንገዴ ብትሄድ፣ ትእዛዜንም ብትጠብቅ፣ ቤቴን ታስተዳድራለህ፤ በአደባባዮቼም ላይ ኀላፊ ትሆናለህ፤ በዚህ በቆሙት መካከል ቦታ እሰጥሃለሁ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል አለው፦ “አካሄድህ እንደኔ ፈቃድ ቢሆን፥ ያዘዝኩህንም ሁሉ ብታደርግ፥ በቤተ መቅደሴ የአስተዳዳሪነትን፥ በአደባባዮቼም የበላይነትን ሥልጣን እሰጥሃለሁ፤ እዚህ ከቆሙት መላእክት ጋር በእኔ ፊት መግባትና መውጣት እንድትችል ባለሟልነትን እሰጥሃለሁ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመንገዴ ብትሄድ ትእዛዜንም ብትጠብቅ፥ በቤቴ ላይ ትፈርዳለህ፥ አደባባዮቼንም ትጠብቃለህ፥ በዚህም ከቆሙት ከእነዚህ ጋር መግባትን እሰጣለሁ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመንገዴ ብትሄድ ትእዛዜንም ብትጠብቅ፥ በቤቴ ላይ ትፈርዳለህ፥ አደባባዮቼንም ትጠብቃለህ፥ በዚህም ከቆሙት ከእነዚህ ጋር መግባትን እሰጣለሁ። See the chapter |