Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘካርያስ 14:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 የግብጽም ወገን ባይወጣ ወደዚያም ባይሄድ፥ ጌታ የዳስ በዓልን ለማክበር የማይወጡትን አሕዛብ የሚቀሥፍበት ቸነፈር በእርሱ ላይ ይመጣል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 የግብጽም ሰዎች ወደዚያ ሳይወጡ ቢቀሩ፣ ዝናብ አያገኙም፤ እግዚአብሔር ወጥተው የዳስ በዓልን በማያከብሩ አሕዛብ ላይ የሚያደርሰውን መቅሠፍት በእነርሱም ላይ ያመጣል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ግብጻውያንም በዓሉን ለማክበር ወደ ኢየሩሳሌም ወጥተው በእግዚአብሔር ፊት መቅረብ ባይፈልጉ፥ “ወደ ኢየሩሳሌም ወጥተን የዳስ በዓል አናከብርም” በሚሉ መንግሥታት ላይ የሚደርሰው ቀሣፊ በሽታ ይመጣባቸዋል።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 የግብጽም ወገን ባይወጣ ወደዚያም ባይመጣ፥ እግዚአብሔር የዳስ በዓልን ያከብሩ ዘንድ የማይወጡትን አሕዛብ የሚቀሥፍበት ቸነፈር በእርሱ ላይ ይሆናል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 የግብጽም ወገን ባይወጣ ወደዚያም ባይመጣ፥ እግዚአብሔር የዳስ በዓልን ያከብሩ ዘንድ የማይወጡትን አሕዛብ የሚቀሥፍበት ቸነፈር በእርሱ ላይ ይሆናል።

See the chapter Copy




ዘካርያስ 14:18
8 Cross References  

በፈረሶች፥ በበቅሎዎች፥ በግመሎች፥ በአህዮች፥ እንዲሁም በዚያም ሰፈር ባሉ እንስሶች ሁሉ ላይ በሰዎች ላይ እንደ ሆነው ዓይነት ቸነፈር በእነርሱም ላይ ይሆናል።


ጌታም ከኢየሩሳሌም ጋር የተዋጉትን አሕዛብ ሁሉ የሚቀሥፍበት ቸነፈር ይህ ነው፤ በእግራቸው ሲቆሙ ሥጋቸው ይበሰብሳል፥ ዐይኖቻቸውም በዓይነስባቸው ውስጥ ይበሰብሳል፥ ምላሳቸውም በአፋቸው ውስጥ ይበሰብሳል።


ይህ የግብጽ ቅጣት ይሆናል፥ የዳስ በዓልንም ለማክበር የማይወጡት አሕዛብ ሁሉ ቅጣት እንደዚህ ይሆናል።


“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገር፦ በዚህ በሰባተኛው ወር ከዐሥራ አምስተኛው ቀን ጀምሮ ሰባት ቀን ለጌታ የዳስ በዓል ነው።


ለአንቺም የማይገዛ ሕዝብና መንግሥት ይጠፋል፥ እነዚያ አሕዛብም ፈጽመው ይጠፋሉ።


እንዲህ ይሆናል፤ በየመባቻውና በየሰንበቱ ሥጋ ለባሽ ሁሉ በፊቴ ለመስገድ ዘወትር ይመጣል፥ ይላል ጌታ።


እጅህ በጠላቶችህ ላይ ትነሣለች፥ ጠላቶችህም ሁሉ ይጠፋሉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements