Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘካርያስ 13:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 በምድርም ሁሉ ላይ ሁለት ሦስተኛው ተቈርጠው ይጠፋሉ፥ ይላል ጌታ፤ አንድ ሦስተኛው ክፍልም በእርሷ ይቀራል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የምድር ሁሉ፣ ሁለት ሦስተኛው ተመትቶ ይጠፋል፤ አንድ ሦስተኛው ግን በውስጡ ይቀራል፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 በአገሪቱ ላይ ካሉት ሕዝቦች ከሦስቱ ሁለቱ እጅ ተመተው ይሞታሉ፤ ሆኖም ከሦስቱ አንዱ እጅ ይቀራል።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 በምድርም ሁሉ ላይ ሁለት ክፍል ተቈርጠው ይሞታሉ፥ ይላል እግዚአብሔር፣ ሦስተኛውም ክፍል በእርስዋ ውስጥ ይቀራል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 በምድርም ሁሉ ላይ ሁለት ክፍል ተቈርጠው ይሞታሉ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ሦስተኛውም ክፍል በእርስዋ ውስጥ ይቀራል።

See the chapter Copy




ዘካርያስ 13:8
34 Cross References  

ከአንቺም አንድ ሦስተኛው በቸነፈር ይሞታሉ፥ በመካከልሽም በራብ ያልቃሉ፥ አንድ ሦስተኛውም በዙሪያሽ በሰይፍ ይወድቃሉ፥ አንድ ሦስተኛውንም ወደ ነፋሳት ሁሉ እበትናለሁ፥ በኋላቸውም ሰይፍ እመዝዛለሁ።


ታላቂቱም ከተማ በሦስት ተከፋፈለች፤ የአሕዛብም ከተማዎች ወደቁ። የብርቱ ቁጣው ወይን ጠጅ የሞላበት ጽዋ እንዲሰጣትም ታላቂቱ ባቢሎን በእግዚአብሔር ፊት ታሰበች።


ጌታ ቀኖቹን ባያሳጥራቸው ኖሮ ማንም ባልዳነ ነበር፤ ስለ መረጣቸው ስለ ምርጦቹ ሲል ግን ቀኖቹን አሳጥሯል።


ከዐሥር አንድ ሰው እንኳን በምድሪቱ ቢቀር፤ እርሱም ደግሞ ይጠፋል፤ ነገር ግን የኮምበልና የባሉጥ ዛፍ በተቈረጠ ጊዜ ጉቶ እንደሚቀር፤ ቅዱሱም ዘር እንዲሁ በምድሪቱ ጉቶ ሆኖ ይቀራል።”


ንጉሡም ተቆጣ፤ ወታደሮቹንም ልኮ እነዚያን ገዳዮች አጠፋ፤ ከተማቸውንም አቃጠለ።


ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፤ በአስማተኞች፥ በዘማውያን፥ በሐሰት በሚምሉ፥ የሠራተኛውን ደመወዝ በሚያስቀሩ፥ መበለቲቱንና የሙት ልጅን በሚያስጨንቁ፥ ስደተኛውን በሚገፉ፥ እኔንም በማይፈሩ ላይ ፈጣን ምስክር እሆንባቸዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።


አንተን ለማዳን ከአንተ ጋር ነኝና፥ ይላል ጌታ፤ አንተንም የበተንሁባቸውን አሕዛብን ሁሉ ፈጽሜ አጠፋለሁ፥ አንተን ግን ፈጽሜ አላጠፋህም፤ እንደጥፋትህ መጠን እቀጣሃለሁ እንጂ ያለ ቅጣት ከቶ አልተውህም።


ወጥተውም በእኔ ያመፁብኝን ሰዎች ሬሳቸውን ያያሉ፤ ትላቸው አይሞትምና፥ እሳታቸውም አይጠፋምና፤ ለሥጋ ለባሽም ሁሉ አስጸያፊ ነገር ይሆናሉ።


ከእናንተም ዘንድ ዓመፀኞችንና የበደሉኝን እለያለሁ። ከኖሩባትም ምድር አወጣቸዋለሁ፥ ወደ እስራኤል ምድር ግን አይገቡም፥ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።


‘ክፉው ነገር አይደርስብንም፥ አያገኘንምም’ የሚሉ የሕዝቤ ኃጢአተኞች ሁሉ በሰይፍ ይሞታሉ።


በመካከልሽ ትሑትና ራሱን ዝቅ የሚያደርግ ሕዝብን አስቀራለሁ፤ በጌታም ስም ይታመናሉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements