ዘካርያስ 10:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 በአንድ ላይም እንደ ጦረኞች ይሆናሉ፥ ጠላቶቻቸውንም በመንገድ ጭቃ ውስጥ የሚረግጡ ይሆናሉ፤ ጌታም ከእነርሱ ጋር ስለሆነ ጦርነት ይገጥማሉ፥ ፈረሰኞችንም ያሳፍራሉ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 ጠላትን መንገድ ላይ እንዳለ ጭቃ ይረጋግጣሉ፤ በአንድነት እንደ ጦር ሰልፈኛ ይሆናሉ፤ እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋራ ስለ ሆነ ተዋግተው፤ ፈረሰኞችን ያዋርዳሉ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 የይሁዳ ሕዝብ ጠላቶቻቸውን ረግጠው ከመንገድ ጭቃ ጋር እንደሚለውሱ እንደ ብርቱ ጦረኞች ይሆናሉ፤ እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋር ስለ ሆነ በርትተው በመዋጋት ፈረሰኞችን ሳይቀር ድል ይነሣሉ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 በሰልፍም ጊዜ ጠላቶቻቸውን በመንገድ ጭቃ ውስጥ እንደሚረግጡ ኃያላን ይሆናሉ፣ እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋር ነውና ይዋጋሉ፥ ፈረሰኞችም ያፍራሉ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 በሰልፍም ጊዜ ጠላቶቻቸውን በመንገድ ጭቃ ውስጥ እንደሚረግጡ ኃያላን ይሆናሉ፥ እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋር ነውና ይዋጋሉ፥ ፈረሰኞችም ያፍራሉ። See the chapter |