This book is not inspired by God and is not part of the Christian canon or the Jewish Tanakh. It is shown only for historical and study purposes. View full explanation መጽሐፈ ጦቢት 2:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 በግንቡ ላይ ድንቢጦች መኖራቸውን አላወቅሁም ነበር፤ ትኩስ ኩሳቸውም በዐይኖቼ ላይ ወደቀብኝና ነጭ ነጥብ ሆነ፤ ለመታከም ወደ ሐኪሞች ሄድሁ፥ ግን መድኃኒት ባደረጉልኝ ቍጥር ነጥቦቹ እየተጨመሩ ሄዱና ጭራሹን ታወርሁ። ለአራት ዓመታት ማየት አልቻልሁም፤ ዘመዶቼም በኔ ነገር በጣም ያዝኑ ነበር፤ አሂካር ወደ ኤሊማይስ እስከሄደበት ጊዜ ድረስ ለሁለት ዓመታት ተንከባከበኝ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 በዕድሞው ላይም ወፎች እንዳሉ አላወቅሁም፤ ፊቴም ተገልጦ ሳለ እነዚያ ወፎች በዐይኔ ላይ የሚያቃጥል ኩስ ጣሉብኝ፤ በዐይኔም ብልዝ ወጣብኝ፤ እኔም ወደ ባለ መድኀኒት ሄድሁ፥ ነገር ግን የጠቀመኝ የለም፤ ብቻዬን ወደ ኤልማድያ እስክሄድ ድረስ አኪአክሮስ ይመግበኝ ነበር። See the chapter |