ሩት 4:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 የቅርብ ዘመዱም፦ “የራሴን ርስት እንዳላበላሽ መውሰድ አልችልም፥ እኔ የራሴ ላደርገው አልችልምና አንተ እንድትወስደው ፈቅጄልሃለሁ” አለው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 ያም ቅርብ የሥጋ ዘመድ፣ “እንዲህ ከሆነማ የራሴን ርስት አደጋ ላይ ልጥል ስለምችል፣ እኔ ልቤዠው አልችልም፤ አንተው ራስህ ተቤዠው” አለው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 ሰውየውም “ይህን ብወስድ የራሴን ድርሻ የሚጐዳ ስለ ሆነ እኔ ልወስደው አልፈልግምና አንተ እንድትወስደው ፈቅጄልሃለሁ” አለው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 የቅርብ ዘመዱም፦ የራሴን ርስት እንዳላበላሽ መቤዠት አልችልም፣ እኔ መቤዠቱን አልችልምና አንተ ከእኔ መቤዠቱን ውሰደው አለ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 የቅርብ ዘመዱም “የራሴን ርስት እንዳላበላሽ መቤዠት አልችልም፤ እኔ መቤዠቱን አልችልምና አንተ ከእኔ መቤዠቱን ውሰደው፤” አለ። See the chapter |