ሩት 1:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 በምትሞቺበት እሞታለሁ፤ በምትቀበሪበትም እቀበራለሁ፤ ከሞት በቀር ከአንቺ የሚለየኝ ነገር ቢኖር ጌታ እግዚአብሔር ይፍረድብኝ!” See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም17 በምትሞቺበት እሞታለሁ፤ እዚያው እቀበራለሁ። ከእንግዲህ ሞት ከሚለየን በቀር ብለይሽ እግዚአብሔር ይፍረድብኝ፤ ከዚህም የከፋ ያድርግብኝ።” See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 በምትሞቺበት እሞታለሁ፤ በምትቀበሪበትም እቀበራለሁ፤ ከሞት በቀር ከአንቺ የሚለየኝ ነገር ቢኖር እግዚአብሔር ይፍረድብኝ!” See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 በምትሞችበትም ስፍራ እሞታለሁ፥ በዚያም እቀበራለሁ፣ ከሞት በቀር አንቺንና እኔን አንዳች ቢለየን እግዚአብሔር ይህን ያድርግብኝ እንዲሁም ይጨምርብኝ አለች። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 በምትሞችበትም ስፍራ እሞታለሁ፤ በዚያም እቀበራለሁ፤ ከሞት በቀር አንቺንና እኔን አንዳች ቢለየን እግዚአብሔር ይህን ያድርግብኝ፤ እንዲሁም ይጨምርብኝ፤” አለች። See the chapter |