ሮሜ 7:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 እንግዲህ ምን እንላለን? ሕግ ኃጢአት ነውን? በጭራሽ! ነገር ግን በሕግ በኩል ባይሆን ኖሮ ኃጢአትን አላውቅም ነበር፤ ሕጉ “አትመኝ” ባይል ኖሮ ምኞትን አላውቅም ነበር። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም7 እንግዲህ ምን እንላለን? ሕግ በራሱ ኀጢአት ነውን? ፈጽሞ አይደለም! ነገር ግን በሕግ በኩል ባይሆን ኖሮ፣ ኀጢአት ምን እንደ ሆነ ባላወቅሁም ነበር፤ ሕጉ “አትመኝ” ባይል ኖሮ፣ ምኞት ምን እንደ ሆነ በርግጥ አላውቅም ነበር። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 እንግዲህ ምን እንላለን? ሕግ ራሱ ኃጢአት ነውን? አይደለም! ነገር ግን ኃጢአት ምን መሆኑን እንዳውቅ ያደረገኝ ሕግ ነው። ሕግ “አትመኝ” ባይል ኖሮ ምኞት ምን መሆኑን ባላወቅሁም ነበር። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 እንግዲህ ምን እንላለን? ኦሪት ኀጢአት ናትን? አይደለችም፤ ነገር ግን ኦሪት ባትሠራ ኀጢአትን ባላወቅኋትም ነበር፤ ኦሪት፥ “አትመኝ” ባትል ኖሮም ምኞትን ፈጽሞ ባላወቅኋትም ነበር። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 እንግዲህ ምን እንላለን? ሕግ ኃጢአት ነውን? አይደለም፤ ነገር ግን በሕግ ባይሆን ኃጢአትን ባላወቅሁም ነበር፤ ሕጉ፦ አትመኝ ባላለ ምኞትን ባላወቅሁም ነበርና። See the chapter |