ሮሜ 7:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 ስለዚህ ባሏ በሕይወት እያለ ሌላ ባል ብታገባ አመንዝራ ትባላለች። ባሏ ቢሞት ግን ከሕጉ ነፃ ናት፥ ሌላ ባል ብታገባ አመንዝራ አይደለችም። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም3 ነገር ግን ባሏ በሕይወት እያለ ሌላ ሰው ብታገባ አመንዝራ ትባላለች፤ ባሏ ቢሞት ግን ሌላ ሰው ብታገባም እንኳ፣ ከዚያ ሕግ ነጻ ትሆናለች፤ አመንዝራ አትባልም። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 ስለዚህ ባልዋ በሕይወት እያለ ሌላ ወንድ ብታገባ አመንዝራ ትባላለች። ባልዋ ከሞተ ግን ከእርሱ ጋር ከታሰረችበት ሕግ ነጻ ትወጣለች፤ ሌላ ወንድ ብታገባም አመንዝራ አይደለችም። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 ስለዚህ ባልዋ በሕይወት ሳለ ለሌላ ወንድ ብትሆን አመንዝራ ትሆናለች፤ ባልዋ ቢሞት ግን ከሕግ ነፃ ወጥታለች፤ ለሌላ ወንድ ብትሆንም አመንዝራ አትባልም። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 ስለዚህ ባልዋ በሕይወት ሳለ ለሌላ ወንድ ብትሆን አመንዝራ ትባላለች፤ ባልዋ ቢሞት ግን ከሕጉ አርነት ወጥታለችና ለሌላ ወንድ ብትሆን አመንዝራ አይደለችም። See the chapter |