Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሮሜ 4:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ለማይሠራ፥ ነገር ግን ኃጢአተኛውን በሚያጸድቅ ለሚያምን፥ እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ይቆጠርለታል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ነገር ግን ለማይሠራ፣ ሆኖም ኀጥኡን በሚያጸድቀው ለሚያምን፣ እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ይቈጠርለታል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ሰው መልካም ሥራ ባይኖረው እንኳ ኃጢአተኞችን በሚያጸድቅ አምላክ ካመነ እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ይቈጠርለታል።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ለማ​ይ​ሠራ ግን ኀጢ​አ​ተ​ና​ውን በሚ​ያ​ጸ​ድ​ቀው ካመነ እም​ነቱ ጽድቅ ሆኖ ይቈ​ጠ​ር​ለ​ታል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ነገር ግን ለማይሠራ፥ ኃጢአተኛውንም በሚያደድቅ ለሚያምን ሰው እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ይቆጠርለታል።

See the chapter Copy




ሮሜ 4:5
24 Cross References  

በክርስቶስም በማመን በእምነት ላይ የተመሠረተውን የእግዚአብሔርን ጽድቅ እንጂ በሕግ ላይ የተመሠረተውን የራሴ ጽድቅ ሳይኖረኝ፥ በእርሱ እንድገኝ ነው፤


ይህ የእግዚአብሔር ጽድቅ ለሚያምኑ ሁሉ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ባለን እምነት የሚገኝ ነው፤ ልዩነት የለምና፤


የእግዚአብሔርን ጽድቅ ባለማወቅ፥ የራሳቸውንም ጽድቅ ለመመሥረት በመፈለግ፥ ለእግዚአብሔር ጽድቅ አልተገዙም።


ለእኛም ጭምር ነው፤ ጌታችንን ኢየሱስን ከሙታን ባስነሣው ለምናምን ለእኛም እንዲቆጠርልን ነው።


መጽሐፉስ ምን አለና? “አብርሃምም እግዚአብሔርን አመነ፤ ጽድቅም ሆኖ ተቆጠረለት።”


ኢየሱስ መልሶ “የእግዚአብሔር ሥራ ይህ ነው፤ ይህም እርሱ በላከው እንድታምኑ ነው፤” አላቸው።


እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘለዓለም ሕይወት አለው፤ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም።


እነሆ፥ እርሱ ኮርቶአል፥ ነፍሱ በውስጡ ቅን አይደለችም፤ ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል።


ኢያሱም ለሕዝቡ ሁሉ እንዲህ አለ፦ “የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘አባቶቻችሁ፥ የአብርሃምና የናኮር አባት ታራ፥ አስቀድመው በወንዝ ማዶ ተቀመጡ፤ ሌሎችንም አማልክት አመለኩ።


ኢየሱስም፥ “የሚቻልህ ከሆነ አልህ? ለሚያምን ሰው ሁሉም ነገር ይቻላል” አለው።


ደግሞም ዳዊት እንኳ፥ እግዚአብሔር ያለ ሥራ፥ ጽድቅን ስለሚቆጥርለት ሰው፥ ስለ መባረኩ ሲናገር፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements