ሮሜ 4:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 እንዴት ታዲያ ተቆጠረለት? ተገርዞ ሳለ ነውን? ወይስ ሳይገረዝ? ሳይገረዝ ነበር እንጂ፤ ከተገረዘ በኋላ አይደለም። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 ታዲያ እንዴት ተቈጠረለት? ከተገረዘ በኋላ ነው ወይስ ከመገረዙ በፊት? የተቈጠረለት ከተገረዘ በኋላ ሳይሆን ከመገረዙ በፊት ነው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 እንግዲህ አብርሃም እምነቱ ጽድቅ ሆኖ የተቈጠረለት መቼ ነው? ከመገረዙ በፊት ነውን ወይስ ከተገረዘ በኋላ? ከመገረዙ በፊት ነው እንጂ ከተገረዘ በኋላ አይደለም። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 ለአብርሃም ጽድቅ ሆኖ የተቈጠረለት መቼ ነው? ተገዝሮ ሳለ ነውን? ወይስ ሳይገዘር? ሳይገዘር ነው እንጂ ተገዝሮ ሳለ አይደለም። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 እንዴት ተቆጠረለት? ተገርዞ ሳለ ነውን? ወይስ ሳይገረዝ? ተገርዞስ አይደለም፥ ሳይገረዝ ነበር እንጂ። See the chapter |