ሮሜ 2:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 ሕግ ሳይኖራቸው ኃጢአት የሠሩ ሁሉ ያለ ሕግ ደግሞ ይጠፋሉና፤ ሕግ እያላቸው ኃጢአት የሠሩ ሁሉ በሕግ ይፈረድባቸዋል፤ See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም12 ሕግ ሳይኖራቸው ኀጢአት የሠሩ ሁሉ ያለ ሕግ ይጠፋሉ፤ ሕግ እያላቸው ኀጢአት የሠሩ በሕግ ይፈረድባቸዋል፤ See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 ሕግ ሳይኖራቸው ኃጢአት የሚሠሩ ሁሉ ሕጉ ባይኖራቸውም ይጠፋሉ፤ ሕግ እያላቸው ኃጢአት የሚሠሩ ሁሉ ግን በሕጉ ይፈረድባቸዋል። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 ከሕግ ወጥተው የበደሉ በሕግ ይፈረድባቸዋል፤ ያለ ሕግ የበደሉ ሁሉም ያለ ሕግ ይፈረድባቸዋል። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 ያለ ሕግ ኃጢአት ያደረጉ ሁሉ ያለ ሕግ ደግሞ ይጠፋሉና፤ ሕግም ሳላቸው ኃጢአት ያደረጉ ሁሉ በሕግ ይፈረድባቸዋል፤ See the chapter |